የድሬድዋ ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ በተለያዩ ዘርፎች ጥናትና ምርምር ማዘጋጀቱን አስታወቀ ::

    ዩኒቨርስቲው በአስተዳደሩ የሚስታወሉ የተለያዩ ማህበራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል ማህ በረሰብ ተኮር ንድፈ ሀሳቦችን በማዘጋጀት ከባለድርሻ ተቋማት ጋር የተጠናቀቁ የጥናትና ምርምር ስራዎች ወርክ ሾፕ አካሄዷል።
    በተዘጋጀው ወርክ ሾፕ ላይ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ተወካይ እና የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን እንደተናገሩት የምርምር ስራዎቻች የማህበበረሰቡን ችግር መፍታት በሚችሉ መልኩ መሰራት እንዳለባቸው ገልፀው ዩኒቨርሲቲው በ2012 የበጀት አመት ፀድቀው ስራ ላይ የነበሩ እና አሁን የተጠናቀቁ አስራ ሶስት (13) የምርምር ስራዎችን ለማስገምገም ወርክ ሾፕ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።
    ዶ/ር ሰለሞን ከዚህም ጋር በማያያዝ የተጠናቀቁ የምርምር ስራዎችም ወደ ቀጣይ ደረጃ ማሳደግ እንደሚገባ በመግለፀ ተሰርተዉ የተጠናቀቁትም ከመደርደሪያ ማሞቂያ የዘለለ ፋይዳ ሊኖራቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
    እንደ ዶክተር ሰለሞን ገለፃ በዩኒቨርሲቲው የተሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች ችግር ፈቼ እንዲሆኑ ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡
    የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተማም አወል በወርክ ሾፕ እንደተናገሩት ተቋማት በዋነኝነት በሚሰሯቸዉ የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት እንደሚለያዩ እና በዚህ መስክ ያለንን ዉስንነት በመፍታት ለማህበረሰቡ ችግር ፈቺ የሆኑ ምርምርና ጥናቶችን በተጠናከረ ደረጃ መሠራት እንደሚገባ ገልገልፀዋል፡፡
    የአስተዳደሩ የገጠር ሴቶች የፍትህ ተደራሽነትን ጥናትና ምርምር ሰርቶ ያቀረበው በዩኒቨርስቲው የህግ ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር እንዳወቅ ፀጋዪ በጥናቱ ለገጠር ሴቶች የፍትሕ ተደራሽነት የሚረዳን ምን አይነት ህግ አለን፣ የፍትህ ተቋማት ለገጠር ሴቶች ምንያክል ተደራሽ ናቸው፣ በቋንቋቸው አገልግሎት ማግኘትንና ያሉበት አካባቢ የመልክዓ ምድር አቀማመጥ በደንብ የዳሰሰ በመሆኑ ወደ ተግባር ሲቀየር ችግር ፈቼ እንደሚሆን ገልፀዋል።
    በወርክ ሾፑ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላትም ዩኒቨርሲቲው እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በማመስገን የተሰሩት ጥናቶች ለማህበረሰቡ ችግር ፈቼ እንዲሆኑ ወደ ተግባር መቀየር አለባቸው በማለት አስተያየታቸውን ሰተዋል።
    ለሁለት ተከታታይ ቀናት በተካሄደው ወርክ ሾፕ ጥናታዊ ፅሁፍ በዋነኝነት በትምህርት ፣ በህግ ፣ በጤና ፣ በተፈጥሮ ሀብት ፣ በስነ-አዕምሮ እና ሌሎች ዘርፎችንም የዳሰሰ ነበረ።
    በወርክ ሾፕ ከዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።