የአስተዳደሩ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለሚዲያና ለህዝብ ግንኙነት ባለሙያዋች ሙያዊ ክህሎትን ለማዳበር ለ6 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ስልጠና መስጠት ተጀምሯል።
በስልጠናው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የኃላፌ ተወካይ አቶ ሚካኤል እንዳለ እንደተናገሩት እንዲህ አይነት ስልጠና ባለሙያዋች በተደጋጋሚ በመጠየቃቸውና በተደረገው የዳስሳ ጥናት መሰረት በማድረግ ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልፀዋል።
በስልጠናው በጠዋቱ ውሎ የኢትዮጰያ ብሮድ ካስት ኃላፊ በዶ/ር ጌታቸው ድንቁ አማካኝነት ኮሚዩኒኬሽን ምንድነው በሚል ርዕስ ለሰልጣኞች ግንዛቤ ተፈጥሯል።


