ለቀጣይ አስር ወራት የሚቆይ ብሄራዊ የወጣቶች በጎ ልማት ተግባራት የሚሳተፉ ሰልጣኞች በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ስልጠና መስጠት ተጀመረ፡፡
ስልጠናው በሰላም ሚንስቴር አዘጋጅነት የተዘጋጀ ሲሆን ትምህርታቸውን ጨርሰው የተመረቁና ወደ ስራ አለም ያልተቀላቀሉ 85 ሺህ ወጣቶች የበጎ ሥራ ተግባራት ለ45 ቀናት የተለያዩ 8 ዩኒቨርሲቲዎች በኦን-ላይን በዛሬው እለት ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል፡፡ የስልጠናውን መክፈቻ ስነ-ስርዓት በንግግር የከፈቱት የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንደተናገሩት በሀገራችን የተለያዩ ባህል፣ እምነትና ማንነት በአንድነትና በመደጋገፍ የሚኖሩ ማህበረሰብ ባላቹ ሞያ በበጎነት ለማገልገል…


