ለቀጣይ አስር ወራት የሚቆይ ብሄራዊ የወጣቶች በጎ ልማት ተግባራት የሚሳተፉ ሰልጣኞች በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ስልጠና መስጠት ተጀመረ፡፡

    ስልጠናው በሰላም ሚንስቴር አዘጋጅነት የተዘጋጀ ሲሆን ትምህርታቸውን ጨርሰው የተመረቁና ወደ ስራ አለም ያልተቀላቀሉ 85 ሺህ ወጣቶች የበጎ ሥራ ተግባራት ለ45 ቀናት የተለያዩ 8 ዩኒቨርሲቲዎች በኦን-ላይን በዛሬው እለት ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል፡፡
    የስልጠናውን መክፈቻ ስነ-ስርዓት በንግግር የከፈቱት የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንደተናገሩት በሀገራችን የተለያዩ ባህል፣ እምነትና ማንነት በአንድነትና በመደጋገፍ የሚኖሩ ማህበረሰብ ባላቹ ሞያ በበጎነት ለማገልገል ቆርጣቹ መነሳታቹ የሀገር ባለ ዉለታ ናቹ ብለዋል፡፡
    የሰላም ሚንስቴር የብሄራዊ በጎ ልማት ሥራዎች ዳይሬክተር ሩት ለማ በበኩላቸው እንደተናገሩት በሀገራችን ሰላም እንዲሰፍን በዋንኝነት የወጣቱ ድርሻ የጎላ ነው ብለዋል።
    ወጣቱ ሀገሩን በማልማት ረገድ ይህ የበጎ ልማት ሥራ ስልጠና ከ45 ቀናት በኋላ ሲጠናቀቅ በመላ የሀገሪቱ ክፍሎች ለ10 ወራት በመንቀሳቀስ ለአቅመ ደካማ፣አካል ጉዳተኛና ሌሎች ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የማህበረሰቡ ክፍሎች የበጎ ሥራ ይሰጣሉ ሲሉ ዳይሬክተሯ ገልፀዋል።
    ይህ የበጎ ልማት ሥራዎች ስልጠና በሀገሪቷ ካሉት 11 ዩኒቨርስቲዎች በተመሳሳይ ሰአት የሚጀመር ሲሆን በዛሬው ቀንም 8 ዩኒቨርስቲዎች በተመሳሳይ ሰዓት በኦን-ላይን ይጀምራሉ፡፡
    በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲም ከ425 በላይ ወጣት በጎ ልማት ሥራዎች ለሚሳተፉ ሰልጣኞች ስልጠናው እንደሚሰጥ ተገልፃል፡፡