አቶ ዩሱፍ ሰዒድ የጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊና የበሽታ መከላከልና ጤና ማበልፀግ ዋና የስራ ሂደት ሃላፊ
በጤና ቢሮና በጤና ተቋማት ላሉና በተለያዩ የስራ ክፍሎች በሃላፊነት እንዲሁም በአስተባባሪነት ለሚሰሩ ሴት ባለሞያዎችና ሰራተኞች የአመራርነት ክህሎት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ስልጠናው በተለይም ባለሞያዎቹና ሰራተኞቹ በሚያገለግሉበት ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዝና ከስራ ባልደረቦቸቸው ጋር በትብብር የመስራት እንዲሁም ስራን የመምራት ክህሎትን እንደሚያዳብርላቸው ሰልጣኞች ገልፀዋል፡፡
የጤናው ዘርፍ እንደሃገርም ሴቶችን ወደ አመራርነት የማምጣት እቅድና ትግበራን በከፍተኛ ሁኔታ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንዳለና በአስተዳደራችንም ይህንኑ ለመተግበር የሚረዱ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ዩሱፍ ሰዒድ ገልፀው በተለያዩ የስራ ሃላፊነቶች ላይ ያሉ ሴቶችም ውጤታማ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
የሴቶችን አመራርነትና ብቃት ለመጨመር በቀጣይም የተለያዩ ስራዎች እንደሚሰሩና በስልጠና፤በከፍተኛ ትምህርት ምችችትና የመሳሰሉትን ማበረታቻዎችን ከአጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰሩ የገለፁት ስልጠናውን ያዘጋጁት የቢሮው የስርዓተ-ፃታና ኤች አይ ቪ ጉዳዮች ባለሞያ ወ/ሮ ምስራቅ ጉሉማ ከጤና ሚኒስቴር ጀምሮ በተለያዩ በመንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ጉዳዩን አስመልክቶ የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
ምንጭ ድሬዳዋ ጤና ቢሮ


