በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከኢፌዴሪ ከተማ ልማትና ቤቶች ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለከተማው ከፍተኛ አመራሮች መልካም አስተዳደር በተመለከተ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

    በስልጠናው መድረክ ለተሳተፉት የአስተዳደሩ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የእንኳን ደህና መጣቹ ንግግር የጀመሩት የአስተዳደሩ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ት ስራ አስኪያጅ ክቡር አቶ አብዱልጀዋድ መሀመድ ድሬዳዋ ምቹና የሰለጠነች ከተማ ለማድረግ እንዲሁም ለእድገቷ እንቅፋት የሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሊረባረብ ይገባል ብለዋል።
    በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስተር ዴኤታ ዶ/ር መስፍን አሰፋ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከሌሎች የዓለም ሀገሮችም ሆነ የአፍሪካ ሀገሮች የከተሜነት ምጣኔዋ ሲታይ
    ዝቅተኛ ቢሆንም በከተሜነት ዕድገት ደረጃ ግን ከሁለት ፋጣን እንደሆነና የዕድገት ምጣኔው በዓመት 5.4 ፐርሰንት እንደሆነ ይነገራል፡፡ በሚቀጥለው 10 ዓመታት የምንተገብረው የሴክተራችን የአስር ዓመት ዕቅድም በ2022 የሀገራችን ከተሞች ነዋሪ ህዝብ ብዛት 44 ሚሊየን እንደሚጠጋ ያሳያል ብለዋል፡፡
    ሚ/ር ዴኤታው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየታየ ላለው ለከተማ እድገት ስታንዳርድና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሁም መልካም አስተዳደርን ያሰፈነ እንዲሆን ሁሉም አመራርና ባለድርሻ አካላት በቂ ግንዛቤ በመጨበጥ ዝግጁ መሆን እንደሚገባቸው ገልጸዋል።
    የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የምዘና ስርዓት ማንዋሎችና መመሪያ እና የህብረተሰብ ተሳትፎ ሰነድ በአቶ ሰለሞን ዳዲ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት ሙያ ስታንዳርዳይዜሽንና የሰው ኃብት ልማት ዳይሬክተር ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
    በውይይቱም ላይ የባለሞያ የግንዛቤ ማሰጨበጫ መድረኮችና የሞያ ብቃት ማረጋገጫ ተግባራት መሰራት እንደሚገባ ተገልጸዋል፡፡