የድሬዳዋ ገቢዎች ባለስልጣን በ6 ወር አፈፃፀሙ 93% እቅዱን ማሳካቱን አስታወቀ፡፡

    የአስተዳደሩ ገቢዋች ባለስልጣን በ6 ወሩ 596 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የእቅዱን 93 በመቶ ማሳካት መቻሉን ለጋዜጠኞች በዛሬው እለት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ፡፡
    የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን የ2ዐ13 የመጀመሪያው 6 ወር የእቅደ አፈጻፀም ዙሪያ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሐመድ በጋዜጣዊ መግለጫቸው እንደተናገሩት
    ተቋሙ በመጀመሪያ 6 ወራት በዝግጅት ምእራፍ በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን በመጥቀስ አሰራሩን ለማዘመን ሰፊ ስራ መስራቱን ገልፀዋል፡፡
    የባለስልጣኑ ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም አክለውም በትግበራ ምእራፍ ባለስልጣኑ ለመሰብሰብ ካቀደው ገቢ ውስጥ ከ596 ሚሊየን ብር በላይ በመሰብሰብ የእቅዱን 93 በመቶ አሳክቷል ብለዋል፡፡ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻፀር የ15 ሚሊየን ብር ብልጫም መመዝገቡንም ገልፀዋል፡፡
    የባለስልጣኑ ዳይሬክተር ከዚህም ጋር አያይዘው እንደ ሀገር የነበሩ ጫናዋችን ውስጥ ሆኖ ይህንን ገቢ መሰብሰብ መቻሉን በመጥቀስ ይህንንም ከግምት በማስገባት መንግስት ለዘርፉ እና ለግብር ከፋዩ በ6ወር ወስጥ 126 የሂሳብ መዝገብ ያዥ የሆኑ ግብር ከፋዮችን በተደረገ ኦዲት ግኝት 76.68 ሚሊዬን ብር ከዚህ ውስጥ በኮሮና ምክንያት በተደረገ ምህረት ወለዱና ቅጣት ተነስቶ 38.11ሚሊዬን ገቢ ሊወሰን በመቻሉ በዚህ ከፍተኛ ድጎማ መንግስት አድርጓል ብለዋል፡፡
    እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ በቀጣይ የማዘጋጃቤታዊ ገቢ መሰብሰብ ላይ ያለውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ከባለድርሻ ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
    የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክቶሬት ባስተላለፉት መልዕክት የአስተዳደሩ የቫት ተመዝጋቢዎች የቀራቸው ጥቂት ቀናት ውስጥ ሪፖርት እንዲያደርጉና መክፈል እዳለባቸውም ገልፀዋል።
    በቀሪዎቹ 6 ወራት ያሉትን ክፍተቶች በማረም በማዘጋጃዊ ገቢ ከመሰብሰብ አንፃር የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ እና የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት እቅድ ሙሉ ለሙሉ ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ ባለስልጣኑ ገልፀዋል፡፡
    በመጨረሻም ለእቅዱ መሳካት አስተዋፅኦ ላደረጉ የአስተዳደሩ ባለድርሻ ተቋማት ፣ለታማኝ ግብር ከፋዮች ፣ ለባለስልጣኑ መስሪያ ቤት አመራርና ባለሙያዋች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
    በትዕግስት ቶሎሳ