የጥምቀት በአል በሰላም እንዲከበር ከፍተኛ አስተዋጾ ላበረከቱ የቀበሌ 06 የማህበረሰብ ክፍሎች የምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

    የመጋላ ፖ/ጣቢያና የቀበሌ 06 አስተዳደር ናቸው ይህንኑ የምስጋና እውቅና ፕሮግራሙን ያካሄዱት::
    የመጋላ ፖሊስ ጣቢያ ሀላፊ ረ/ኢ/ር ሳራ ተሰማ በፕሮግራሙ ላይ ባሰሙት ንግግር በቀጠናው በተለያዩ የጸጥታ ስራዎች ላይ ህብረተሰቡ እያደረገ ያለው አስተዋጾ ተኪ የለሽ መሆኑን ገልፀው የዘንድሮው የጥምቀት በአል በሰላም ተከብሮ እንዲያለፍ የአካባቢው ማህበረሰብና የመንደር ኮሚቴዎች ላደረጉት ድጋፍና እገዛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል::
    የቀበሌ 06 የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሳላህ ኢብራሂም በበኩላቸው ህብረተሰቡ የጥምቀት በአል በሰላም እንዲከበር ለደረገው አስተዋጾ አመስግነው ህግ አስከባሪው ያለ ህብረተሰቡ ተሳትፎና ድጋፍ ሰላምን በበቂ ሆኔታ ማረጋገጥ የማይቻል በመሆኑ ይሄው እገዛና ድጋፍ በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል::
    በእለቱ ለጥምቀት በአል በሰላም መከበር እገዛና አስተዋፆቸው ከፍተኛ ለሆኑ የህ/ብ ክፍሎች በጣቢያውና የቀበሌ በጋራ የምስጋናና የዕውቀና ስነ ሰርዕት አካሄደዋል።
    ምንጭ፦ ድሬ ፖሊስ