ሉሲ ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በቀንና በመታው መረሐ ግብር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

    በምርቃ ሰነስረአቱላይ የኮሌጁ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መቅደስ መሐሪ በ1994 ወደስራ የገባወ ኮሌጁ ከጊዜ ወደ ጊዜ የማስተማር ጥራቱን እያሻሻለ መዝለቁን ተናግረዋል።
    በ2013 ዓም በቢዝነስ አድምንስትሬሽን በመስተርስ ዲግሪ ኘሮግም ለማሰልጠን ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ፈቃድ ማግኝቱን ጠቁመዋል።ከፍለው ለመማር የማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የትምህረት እድል በመስጠት በዘርፉ የሚጠበቅበትን የማህበራዊ አገልግሎት ሐላፊነት እተወጣ መሆኑን ፕሬዝዳንቷ ገልፀዋል።
    ዩንቨርስቲ ኮሌጁ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ከ25 ሸህ በላይ ዜጎችን አስተምሮ ማስመረቁን በዛሬው እለት በዲግሪ መረሐ ግብር በአኮውንቲንግ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን በነርሲንግ እና በኮምፒውተር ሳይንስ
    *152 ወንድ
    *279 ሴት በድምሩ 431
    አንደዚሁም በደረጃ አራት
    *43 ወንድ
    *203 ሴት በድምሩ 246
    በአጠቃላይ በሁለቱም መረሐ ግብር /ማለትም በድግሪና በደረጃ አራት/ 677 ተማሪዎችን ለማስመረቅ እንደቻለ ከአጠቃላይ ተመራቂዎች 70 በመቶ እሴቶች መሆናቸውን ፕሬዝዳንቷ ወ/ሮ መቅደስ መሐሪ አስረድተወል።
    በስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ አህመድ መሐመድ ቡህ ዩንቨርስቲ ኮሌጁ በየደረጃው የሚያስፈልገውን የተማረ የሰው ኃይል በማፍራት እረገድ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ አመስግነዋል።ተመራማሪዎች በቀጣይ በሰለጠበት ዘርፍ አገርና ወገን የሚጠቅም ስራ በታማኝነት እንዲሁም በቅንነት ለማገልገል መዘጋጀት እንደሚገባቸው መልእክት አስተላልፈዋል።
    ዛሬ ለምርቃት የበቁት ተማሪዎች በአለማቀፍና በአገራችን በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት መመረቅ ከሚገባቸው ጊዜ ዘግይተው መመረቃቸውን ለማወቅ ተችሏል።