በድሬዳዋ አስተዳደር ለስምንት ቀን የተካሄደው የ2013ዓም የኢትዮጵያ ቴኒስ ሻምፒዮና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡
– # በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች መካከል በድሬዳዋ ከተማ በተካሄደው የኢትዮጵያ ቴኒስ ሻምፒዮና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁለቱም ፆታ ሁለት ዋንጫዎችን በማግኘት አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል ።
# ውድድሩን ላስተናገደው የድሬዳዋ አስተዳደር ለስኬታማ ዝግጅቱ ዋንጫ ተሸልሟል ፡፡
# ኦሮሚያ በሁለቱም ፆታ በሁለተኛነት በማጠናቀቁ የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሲሆን ድሬዳዋ እና የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/ በሴቶች እና ወንዶች 3ኛ በመሆን የነሐስ ሜዳሊያ ሽልማቶችን ከኢ.ፊ.ድ.ሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር እና ከሌሎች ተጋባዥ እንግዶች የዋንጫ ፡ የሜዳሊያና ልዩ ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል ፡፡
#የድሬዳዋ አስተዳደር ለተሳታፊዎች የምስጋና ልዮ ስጦታ በኮሚሽነሩ ሻኪር አህመድ ተሰጥቷቸዋል ፡፡
# በሻምፒዮናው ከአራት ክልሎችና ከሁለት ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ወንድ 30 ሴት በድምሩ 60 ስፖርተ ተጫውተዋል።
# ምንጭ ከድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሸን ኮሚኒኬሽን


