በድሬዳዋ አስተዳደር የቀበሌ 02 ብልጽግና ፓርቲ ለተወካዮች፣ ለከተማና ለቀበሌ ም/ቤት እጩ ተወዳዳሪዎች በማቅረብ ከህብረተሰቡ ጋር የማስተቸትና የውይይት መድረክ አካሄደ።
የማስተቸትና የውይይት መድረክ የተካሄደው በሁለት መሰብሰቢያ አዳራሽ የቀበሌውን ነዋሪዎች በመክፈል ሲሆን አስተዳደሩን ወክለው በእጩነት የቀረቡ 2 የተወካዮች ም/ቤት እጩዎች፣ 9 ለከተማና 300 ለቀበሌው ም/ቤት እጩ ተወዳዳሪዎች ቀርበው ህብረተሰቡን የማስተቸት ስራ ተከናውኗል። መድረኩ በቀበሌው ድጋፍ ሰጪ አመራሮችና የፓርቲው አስተባባሪዎች ተካሂዷል። በትላንትናው እለት ተመሳሳይ መድረኮች በ8 ከተማ ቀበሌዎችና በ4 ገጠር ክላስተሮች ተከናውኗል። ምንጭ፦# DD #PP


