በድሬደዋ ከተማ በተካሄደዉ መድረክ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያስተላለፉት በፌደራልትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ት ኃላፊ ወሮ ሰአዳ አዋሌ እንደተናገሩት የሞተር አልባ ትራንስፖርትና የእግር ጉዞን ማህበረሰቡ እንደባህል እንዲጠቀም ለማበረታታት በየወሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው መርሀግብር እንደ ድሬደዋ በማህበረሰቡን በመነቃቃት ለውጥ እያመጣ እንዳለ ጠቁመዋል፡፡
በዚሁ በትራንስፖርት ሚኒስትርና ትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትበቅንጅት በሚዘጋጀው መርሀግብር በየወሩ የሳታፊ ቁጥር እየጨመረ እዳለ የጠቆሙት ወ/ሮ ሰአዳ በቀጣይም ማህበረሰቡን ይበልጥ ለመድረስ መርሀግብሩን ከቀበሌዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት እንደሁም መርሀግብሩ ሚካሄድበትን ቦታ ለማህበረሰቡ በቀረቡ ቦታዎች በማድረግ ይበልጥ ተደራሽ ለመሆን እንሰራለን ብለዋል፡፡
በመርሀግብሩ ላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችና የእግርና ሳይክል ጉዞ ተከናውኗል፡፡
መረጃው የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከሚዩኒኬሽን ነው፡፡


