የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት በአስተዳደሩ ከሚገኙ ባለሀብቶች ጋር የምክክርና ሀብት የማሰባሰብ መድረክ አካሄደ::

    ሀገር ከድህነት ቀንበር እንድትወጣና ልማቷ በአስተማማኝ ደረጃ ላይ ደርሶ የዜጎች ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ከመንግስት ቁርጠኛ አመራርና ከህዝቦች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ባሻገር የባለሀብቶች ሚና ከፍተኛ ቦታ የሚይዝ መሆኑን የአስተዳደሩ ም/ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ መድረኩን በከፈቱበት ጊዜ ተናግረዋል።
    የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ የፓርቲውን ጥቅል ዓላማ፣ መለያ ዕሴቶች፣ የፖለቲካ ፕሮግራም፣ የኢኮኖሚ ፕሮግራም፣ ማህበራዊ ፕሮግራም እና የውጭ ግንኙነት ፕሮግራም ሰነድ የሀብት ማሰባሰብ ልዩ የእራት ፕሮግራም ላይ ለተገኙ የአስተዳደሩ ባለሀብቶች አቅርበዋል።
    በማጠቃለያው ለመሰብሰብ ከታቀደው ብር 10 ሚሊየን 9 ሚሊዮን 52 ሺ ቃል በማስገባት የእለቱ መርሃግብር ተጠናቀቀ።