በድሬዳዋ አስተዳደር የቀበሌ 02 ብልጽግና ፓርቲ ለተወካዮች፣ ለከተማና ለቀበሌ ም/ቤት እጩ ተወዳዳሪዎች በማቅረብ ከህብረተሰቡ ጋር የማስተቸትና የውይይት መድረክ አካሄደ።

    የማስተቸትና የውይይት መድረክ የተካሄደው በሁለት መሰብሰቢያ አዳራሽ የቀበሌውን ነዋሪዎች በመክፈል ሲሆን አስተዳደሩን ወክለው በእጩነት የቀረቡ 2 የተወካዮች ም/ቤት እጩዎች፣ 9 ለከተማና 300 ለቀበሌው ም/ቤት እጩ ተወዳዳሪዎች ቀርበው ህብረተሰቡን የማስተቸት ስራ ተከናውኗል።
    መድረኩ በቀበሌው ድጋፍ ሰጪ አመራሮችና የፓርቲው አስተባባሪዎች ተካሂዷል።
    በትላንትናው እለት ተመሳሳይ መድረኮች በ8 ከተማ ቀበሌዎችና በ4 ገጠር ክላስተሮች ተከናውኗል።
    ምንጭ፦# DD #PP