መልዕክተ ድሬ 703

    ከተመዘገበው አስገራሚ ድል ምን እንማራለን?

    አብረን በኖርንባቸው ባለፉት አያሌዓመታት ያካበትናቸው የመቻቻል፣ የአብሮነትና
    በሀገር ጉዳይ ላይ የአትንኩን ባይነትእሴቶቻችንን በየጊዜው ልናድሳቸውና ለመጪውትውልድ በአደራ ልናሻግራቸው ይገባል፡፡እነዚህና ሌሎችም እሴቶቻችን በፍቅር፣በይቅርታ እና በመደመር የሚገነባውን ጠንካራ
    አንድነታችንን የበለጠ የማጠናከር ኃይልስላላቸው የአሁኑ ትውልድ ትምህርት ሊወስድባቸው ይገባል፡፡…..ለበለጠ መረጃ ገፅ 3 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ7 0 3

    ልዩነቶቻችን ውበት እና መብቶቻችን እንጂየግጭት መንስኤዎች ስላልሆኑ ልንጠነቀቅ ይገባል

    ልዩነቶች ከነባራዊ ሁኔታዎቻችን አሊያምከዝንባሌዎቻቻንና ከፍላጎቶቻችን የሚመነጩ
    የማንነታችን መገለጫዎች ናቸው ፡፡ ከዚህ አንጻር ምንም ዓይነት ልዩነቶች ከተፈጥሯዊ
    ማንነታችንና ከዕምነታችን ስለሚመነጩ በአስተሳሰብና በተግባራችን ሊገለጡ ይችላሉ ፡፡
    እነዚህ ልዩነቶቻችን አንዳንዶቹ ገና ከጠዋቱ ስንወለድ ጀምሮ አብረውን የነበሩ በመሆናቸው
    ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ከጊዜ በኋላ በመኖር ሂደት አምነገንባቸው የተቀበልናቸው ስለሆኑ
    ከማንነታችን ጋር በእጅጉ የተቆራኙ ናቸው፡፡….ለበለጠ መረጃ ገፅ 3 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ7 0 3

    የሱዳን የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ዛሬ ለምን?

    ሱዳን 1972 ከተደረገው ስምምነት ወዲህ የመሬት ጉዳይ ከኢትዮጵያ አጋጭቷት አያውቅም ነበር።ህወሃት ኢትዮጵያ ላይ ስልጣን ከጨበጠ ወዲህ ግን የመሬት ጥያቄ እንደገና አነሳች፡፡በጣም የሚደንቀው ሱዳን የኢትዮጵያ ይዞታ እና የትግራይ ይዞታ በማለት አገራችንን እንደሁለት መቁጠር መጀመሯ ነበር።ህወሃት ጉልበት ስር መተዳደር የጀመረውን የሁመራ-ልጉዲ አካባቢ የትግራይ ስለሆነ የይገባኛል ጥያቄዋን ተወች፡፡በምትኩ ሱዳን ወዳጄ የምትላትን የትግራይን ይዞታዎች በመተው ከትግራይ ይዞታ ውጭ ያሉትን የኢትዮጵያ መሬት ወረረች፡፡ለምን ? ለሚለው ጥያቄ የምናገኘው አሳዛኝ ምላሽ ‘ህወሃት አገራችንን ወክሎ ከሱዳን ጋር የተፈራረማቸው የክህደት ስምምነቶች መኖራቸው ነው።…….ለበለጠ መረጃ ገፅ 10 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ7 0 3