በስርዓተ-ምግብ አለመስተካከል የሚከሰቱ ማህበራዊ ችግሮችን ለመከላከል ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ::

    በብሔራዊ የሥርዓተ ምግብ ፖሊሲ፣ የህፃናት የመጀመሪያ 1ሺ ቀናት እና በጤናማ እናትነት ዙሪያ
    ለድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት ዛሬ የካቲት 5 በተካሄደ የግንዛቤ ማዳበሪያ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የምክር ቤቱ አባላት ለወከሉት ህብረተሰብ ህፃናት የተመጣጠነ ምግብ በአግባቡ ካለማግኘታቸዉ የተነሳ ለአካላዊ የመቀንጨር ችግር እንደሚጋለጡ እና ይህን ለመከላከል በቀላል ዋጋ የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ የችግሩን ለመከላከል ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቅሰዉ በስርዓተ-ምግብ አለመስተካከል የሚከሰቱ ማህበራዊ ችግሮችን ለመከላከል ሁሉም የበኩሉን ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅተዉ የበኩላቸዉን ድርሻ እንዲወጡ በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
    የድሬ ደዋ ጤና ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ በበኩላቸዉ ለህፃናት አካላዊና አዕምሯዊ እድገት የእርግዝና ወቅትን ጨምሮ በመጀመሪያዎቹ 1000 ቀናት ዉስጥ የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
    በመድረኩ ላይ በብሔራዊ የሥርዓተ ምግብ ፖሊሲ፣ የህፃናት የመጀመሪያ 1ሺ ቀናት እና በጤናማ እናትነት ዙሪያ መጀመሪያዎቹ 1000 ቀናት ዙሪያ ፁሁፎች ቀርበዋል፡፡
    የእርግዝና ወራትዘጠኝ ወር ከ5 ቀን በድምሩ 275 ቀናት ፣ የተወለደው/ችው ህፃን 6 ወር እስኪሞላው/ላት ያለው ጊዜ 6 ወር በድምሩ 180 ቀናት እና የተወለደው/ችው ህፃን ከ6 ወር አንስቶ ሁለት አመት እስኪሞላው ያለው ጊዜ በድምሩ 545 ቀናት ናቸው፡፡
    የተመጣጠነ ምግብ የማያገኙ ህፃናት ለአካላዊ መቀንጨርና ለአዕምሮ እድገት ዉስንነት ስለሚጋለጡ የትምህርት አቀባበላቸዉና በተሰማሩበት የሥራ መስክ ምርታማነታቸዉ ዝቅተኛ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
    የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለአካላዊ እድገት መቀንጨር ከማጋለጡም በተጨማሪ በርካታ ህፃናትን ለህመምና ሞት የሚያጋልጥ፣ በሀገር ኢኮኖሚ እድገት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳርፍ ችግር በመሆኑን በመድረኩ ላይ ተብራርተዋል ፡፡