በዛሬው እለት በሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ተመራቂ የሆኑ አባላትም ወደ ደቡብ ሱዳን የሚሰማሩ የ15 ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ሲሆኑ አለም-አቀፍ ግዳጅን መወጣት የሚያስችላቸውን የስልጠና ዝግጅት ማድረጋቸውም ታውቋል።
በሰላም አሰከባሪዎቹ የምረቃ ስነ-ስርአት ላይም በኢ.ፌ.ድ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር የኢንዶክትርኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማ እና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ እስቂያስ ታፈሰ ተገኝተዋል።


