በ 8 ተኛው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራዎች ላይ ነዋሪዎች ብሎም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በጋራ በመሆን መስራት እንደሚገባቸው ተገለፀ ።

    የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ውሀ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ 8 ተኛውን የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራዎችን አስመልክቶ የክላስተርና የቀበሌ ደጋፊ አመራሮች ተሳታፊ የሆኑበት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል ።
    በግንዛቤ ማስጨበጫው ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ከድር ጁሀር ከዚህ ቀደም የተሰሩ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራዎች አሁን ላይ ያሉበትን ደረጃ በየቀበሌ ከመገምገም በዘለለ በነገው እለት በይፋ በሚጀመረው የተፋሰስ ልማት ስራዎች ላይ በተቀናጀ መልኩ መስራት እንደሚገባ አቶ ከድር ተናግረዋል ።
    የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራዎች በነገው እለት በድሬዳዋ በሚገኙ በሁሉም ክላስተሮች በይፋ እንደሚጀመር የግብርና ውሀ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ተናግረው ከተፋሰስ ልማት ስራዎች ጎን ለጎንም ለሀገራዊ ምርጫው ቅስቀሳ እንደሚደረግም አቶ ኢብራሂም ተናግረዋል ።
    ዘንድሮ የሚካሄደው የተፋሰስ ልማት ስራ ከሀገራዊ ለውጡ ጋር ተያይዞ ከመካሄዱም ባለፈ በቀጣይ ከሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ጋር መገጣጠሙ የተፋሰስ ስራውን ለየት እንደሚያደርገው የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ የልማታዊ ተቋማት ክትትልና ድጋፍ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ኡመር አህመድ ተናግረዋል ።