ትክክለኛና ምክኒያታዊ እንድንሆን
መረጃን ከእውነተኛ ምንጭ እንውሰድ
ማንኛውም ሀገር ወዳድ ዜጋ በማህበራዊው፣ በኢኮኖሚውና በፖለቲካው በንቃት ተሳትፎ ለሀገሩ አንዳች አስትዋጽዖ ማበርከት ይፈልጋል፡፡ ይህንን የተቀደሰና ከሀገር ፍቅር የሚመነጭ ፍላጎት ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ እና ቀጣይ እንዲሆን ለማድረግ ትክክለኛና ከምንጩ የተቀዳ መረጃ ያስፈልገናል፡፡ ምክኒያቱም ስለራሳችንም ሆነ ስለሀገራችን ትክክለኛና ተገቢ ውሳኔ ለመወሰን በትክክለኛ መረጃ ላይ መመስረት ስለሚገባ ነው፡፡
አሁን እንደሀገር እና እንደ ህዝብ የምንገኝበት ተጨባጭ ሁኔታ እንደሚያመላክተው ከሆነ እያነዳንዱ ዜጋ በሰከነና ማስተዋል በተሞላበት መንግድ በምክኒያት መደገፍና በምክኒያት መቃወም ወይም መንቀፍ እንደሚገባው ነው፡፡ ይህ በእጅጉ የሚጠቅመው በብዙ መስዋዕትነት የተገኘውን ይህንን የለውጥ ሂደት እንደ አንድ መላካም ዕድል በመጠቀም ለሀገር እንዲጠቅም ለማድረግ ነው፡፡ ይቀጥላል…ለበለጠ መረጀጃ ገፅ 3 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ7 1 0
በአድዋ እና እኛ
አፄ ምኒልክና በተቀሩት ጀግና የጦር መሪዎቻቸው የሚመራው የኢትዮጵያ ወታደር በወራሪው ጣሊያን ላይ ድል ከተቀዳጀ ይኸው 125 ዓመት ሆነው። ከረጅም ዓመታት ጀምሮ የአድዋ በዓል በየአመቱ ይከበራል። በአሁኑ ወቅት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህንን ታላቅ የድል በዓል ያከብራል። አገሩን ከሚወደውና አዲስ ኢትዮጵያን በጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባት ከሚፈልገው ጀምሮ፣ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ከውጭ ኃይሎች ጋር በማበር ዛሬ አገራችን የምናየው ውድቀት ውስጥ እንድትወድቅ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ለማበርከት እስከበቃው ድረስ፣ ሁሉም በየፊናው ይህንን በዓል ያከብራል።
አድርባዩ፣ የማርክሲዝምን አርማ አንግቦ ወጣቱን ያሳሳተውና ለብዙ ሺዎች ወጣቶች መሞት ተጠያቂው እስከሆነው ድረስ፣ ካለምንም ምህረት ወጣቱን በመጨረስ የሚታወቀው ወታደራዊ አገዛዝና ሌሎች ሺህ በሺህ የሚቆጠሩ አድርባዮችና፣ የአድዋን ድል ትርጉም በደንብ ያልተረዳውና ግራ የተጋባው፣ በኢትዮጵያዊነትና በአሜሪካዊነት መሀከል የሚዋልለው ሁሉና፣ ባንዲራውን ረግጦ ከወጣ በኋላ ”የዚህች ባንዲራዬ ነገር“ እያለ ወጣቱን የሚያሳስተው ሁሉ፣ ሁላችንም አባቶቻችን በወራሪው ጣሊያን ላይ የተቀዳጁትን ድል በማስታወስ እንኮራለንም፡፡ ይቀጥላል…ለበለጠ መረጀጃ ገፅ 10 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ7 1 0
ዘሪና አጫጅ
ሰማያትንና ምድርን የፈጠረው ፈጣሪ የምድር ባዶነት አልመችህ ቢለው የተለያዩ ፍጥረታትን አከለባት፡፡ ሆኖም ግን አሁንም የምድር ባዶነት እንጂ ሙላቷ አልታይህ ስላለው አዳም የሚባል ጎልማሳ ከምድር አፈር አበጀና እስትንፋሱን እፍ አለበት ይላሉ የዕምንት መጻህፍት ፡፡ አሁንም ምድርን ለመሙላት አዳም ብቻውን በቂ ስላልሆነ ሄዋንን ከጎድን አጥንቱ አበጀለት አሁን የፈጣሪ ዐይኖች ወደ ሰው ልጆች ሆኑ፡፡ የሰው ልጅ ከማንኛውም አለማዊ ፍጡር ሰብአዊ በመሆኑ የሚሰጠው ቦታ ከፍተኛው ነው ለዚህ ደግሞ ማስረጃው ከሱ ውጪ ያሉ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ትዕዛዝ መውጣቱ በቂ ምስክር ነው፡፡
ይህ የሰው ልጅ ገና ከፅንሰቱ ጀምሮ የተስተካከለ የዕድገት ቁመና ይኖረው ዘንዳ አቅም እንደሚፈቅደው፣ ባህል እንደሚለውና ሀይማኖት እንደሚያዘው እንደ ፈርጅ እንደ ፈርጁ ፅንሱን ከቋጠረችዋ እናት ጀምሮ በተለያዩ አካላት ነገ ሀገር ለሚሆኑት ማሙሽና ሚሚ እንክብካቤ ይደረጋል፡፡ ዋናው ቁም ነገር ግን እንክብካቤው እስከየትኛው የህጻናቱ ዕድሜ ይቀጥላል የሚለው ነው ለዚህ ጥያቄ መነሳት ምክኒያቱ አልፎ አልፎ በሀገራችን የሚታየውን የልጆችና የወላጆች ግንኙነትን መሰረት በማድረግ ነው፡፡ ይቀጥላል …ለበለጠ መረጀጃ ገፅ 4 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ7 1 0


