ይህን የግንዛቤ ማዳበሪያ በንግግር የከፈቱት የአስተዳዳሩ ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ ቡህ በመክፈቺያ ንግግራቸው የመንግስት አገልግሎት ዘርፍ በብቃት ላይ የተመሰረተ እና ነፃ ተወዳዳሪ ፣ ገለልተኛና ብቃት ላይ የተመሰረተ እና ወደ ተሸለ ደረጃ ለማድረስ የሀገራዊ ሪፎርሙ አንድ አካል መሆኑን ገልፀው የመድረኩ ተሳታፊዎች ከዚህ የሚያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር እንድትለወጡ በማለት መልእክት አስተላልፈዋል ፡፡
በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋዬ በላቸው እንደተናገሩት መንግሥታችን የሀገራችንን የመንግሥት አገልግሎት ዘርፍ ነፃ፣ ገለልተኛና ብቃት ያለው አድርጎ ለማደራጀት የለውጥ ፍኖተ-ካርታ ቀርፆ ሰፊ የህግ ድጋፍ የማይፈልጉ የለውጥ ፕሮጀክቶችን በሪፎርም አመራር አግባብ በሁሉም የሲቪል ሰርቪስ ተቋማት፣ በፌዴራልና በክልሎች እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎቻችን ለመተግበር ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልፀው ይህ የለውጥ ፍኖተ-ካርታ አራት ትልልቅ ፕሮግራሞችን ያካተተ ሲሆን፤ እነዚህም፦ ነፃ፣ ገለልተኛና ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ግንባታ፣ የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ሥርዓት፣ የእሴት ግንባታና ሥነ ምግባር፣ ውጤታማ የመንግሥት አገልግሎት ሥርዓት ግንባታ ናቸው።
የድሬ ደዋ አስተዳዳር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ አቡበከር አዶሽ በበኩላቸዉ የዓለም ሀገራት የደረሱበት የዕድገት ደረጃ ላይ ሀገራችንን ለማድረስ ሲቪል ሰርቫንቱ የኩሉን ድርሻ እንዲወጣ በአመለካከት እና በተግባር ለመገንባት ታስቦ ከፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በተገኘ ድጋፍ ይህን የግንዛቤ ማዳበሪያ መዘጋጀቱን አብራርተዋል፡፡ የግንዛቤ ማዳበሪያ መድረኩ ዛሬ በመቀጠል ሰፊ ውይይቶች ይካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡


