ሴቶች የማህበረሰብ
ድርሻቸውን በሚገባ ሊወጡ ይገባል
ሴቶች በማህበረሰቡ መሀል ያላቸው የመምራት ኃላፊነት ድርሻ ድርብ እና ከፍተኛ ነው፡፡ ይህ ኃላፊነት የሚጀምረው የሀገር እና የህዝብ መሠረት የሆነው ቤተሰብ ውስጥ ነው፡፡ ቤተሰብን መምራት ምን ያህል አንደሚከብድ የሚታወቀው በሆነ አጋጣሚ የቤተሰብ አስተዳዳሪ የሆኑት ሴቶች ከቤተሰብ ተለይተው ሲቆዩ ነው፡፡ ለዚህ ዋና እማኝ የሚሆኑት ሁኔታው ያጋጠማቸው አባወራዎች ናቸው፡፡
የሴቶች የመምራትና የኃላፊነት ድርሻ በቤተሰብ ውስጥ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ የቤተሰቡንም የወጪ ክፍተት ለመሸፈን በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ በሚያደርጉት ጥረትና የቤተሰቡን ወጪ በማብቃቃት እና በታማኝነት መምራት ላይም በግልጽ የሚታይ ነው፡፡ ስለዚህ ሴቶች የአንድ ቤተሰብ የጀርባ አጥንት ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ይቀጥላል…ለበለጠ መረጃ ገፅ 3 ያንብቡመልዕክተ ድሬ7 1 4
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል
ማንበብ በጣም ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡አብዘሀኛውን ጊዜ የሚያነቡ ሰዎች በሁሉ ነገር ሙሉ ናቸው ተብሎ ይታሰባል፡፡ እንደማያነቡ ሰዎች አይደሉም በተፈለገው ቦታ ቢገኜም ስጋት አይገባቸውም ምክንያቱም ከእነሱ የሚፈለጉ ነገሮች እንዳሉ ይረዳሉ፡፡ሌላው ምንባብ በጣም ሰው ይቀይራል፡፡ ካነበብነው ውጪ ሌላ ነገር ያለ እስከማይመስለን ድረስ ይለውጣል፡፡የማንበብን ጠቀሚታ የተረድ ሰዎች አብዘኛውን ጊዜ የነሱ ጓደኛ መጸሀፍ ብቻ ነው፡፡ ለምን ቢባል ጠቀሜታው አስቀድምው ካነበቧቸው መጽሀፎች ተረድተዋል፡፡
በነገራችን ላይ አንድ ነገር ትዝ አለኝ በሰፈራችን የተጣላን ሰው በማሰታረቅና የምንባብን ጠቀሚታ ጠንቅቀው የሚያውቁ የጓደኛዬ አያት ነበሩ የተጣሉትን ሰው ሁሉ አሰታረው ሲጨርሱ አንብቡ የወደቀ ወረቀትም ቢሆን አትለፉት አንስታችሁ አንብቡት ማለታቸውን አይተውም ነበር፡፡ ታዲያ በአካባቢው የነበራቸው ቅጥያ ሰም እማማ መጽሀፍ ይባሉ እደነበር አስታውሳለሁ፡፡ የማያነብ ሰው “ለጸብ ቅርብ ነው፡፡” “ስቶ ያሰታል፤” ይሉናል ፡፡ “ትንሹንም ትልቁንም ሰው እንደፈለገ ለመዝለፍ ይሞክራል፡፡” ለሱ ጠብ እንደትክክለኛ መፍትሄ አድርጓ ይጠቀምበታል ባይ ናቸው፡፡ ይቀጥላል…ለበለጠ መረጃ ገፅ 2 ያንብቡመልዕክተ ድሬ7 1 4
ክብር ለመከላከያ ሠራዊታችን!
ጀግናው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ወደድነውም ጠላነውም የአገር መከታ፣ የሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ጠባቂ ነው፡፡ ዘር፣ ሃይማኖትና ሌላው ጉዳይ ሳይለያየው ለሰንደቅ ዓላማውና ለመላው ሕዝብ በእኩልነት እንደሚያገለገል የታመነ ነው፡፡ ትናንትም ሆነ ዛሬ የውጭ ኃይል ጥቃትን በመመከትና ጦርነትን በማስቀረት በኩል ሚናው ከፍተኛ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ በቅርብ ጊዜም ሆነ ከዚያ በፊት በአገር ውስጥ በተዛባ የፖለቲካ ውዝግብ ወይም በጽንፈኞች ቅስቀሳ በሕዝብና በአገር ላይ የሚቃጣ ማንኛውንም ጥቃት በመመከትና አገርን በማረጋጋት ረገድ ታሪካዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው፡፡ በዚህ ተግባሩ ደግሞ መቼም ቢሆን መከበርና መመሥገን ነው ያለበት፡፡ በእርግጥ የእኛ ሠራዊት አይደለም በአገር ውስጥ፣ በውጭ የሰላም ማስከበር ግዳጆችም በጠንካራ የሕዝብ አገልጋይነት፣ ለተጎጂዎች አለኝታ የመሆን ዲስፒሊን ያለውና የነበረው እንደሆነ የተመሰከረለት ነው፡፡ የእኛን አገር ጨምሮ በብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች የሚታየው የብሔር ሽኩቻና የሥነ ምግባር ጥሰት የማይታይበትና በፈረጠመ የሕዝቦች አንድነት ተምሳሌትነቱን የሚታወቅ ነው፡፡..ይቀጥላል…ለበለጠ መረጃ ገፅ 6 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ7 1 4


