በድሬዳዋ አስተዳደር የድልጮራ ጄኔራል ሆስፒታል የሚሰጠውን አገልግሎት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ እንዲቻል ዉይይት ተካሄደ::

    የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ እና የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሱልጣን አሊዪ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሀላፊ ወ\ሮ ለምለም በዛብህ ፣አስተዳደሩ እና የፌደራል የጤና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት አስተዳደር የድልጮራ ጄኔራል ሆስፒታል የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ እንዲቻል በተዘጋጃ የጥናት ዕቅድ ላይ ምክክር ተካሄደ፡፡
    በዚህ የምክር መድረክ ላይ የመክፈቺያ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ እና የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሱልጣን አሊዪ አንዳሉት የድልጮራ ጄኔራል ሆስፒታል ለምስራቁ የሀገራችን ክፍል ህዝቦች የጤና አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ በሀገራቀፍ ደረጃ በ24 የሀገራችን ሆስፒታሎች የአይ ኬር ፕሮግራም ከመጀመሪባቸው አንዱ የድልጮራ ጄኔራል ሆስፒታል መሆኑ ትክክለኛ እና የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ የሚተገበረው ይህ ፕሮግራም ለበርካታ ዜጎች የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት እንዲሻሻል የሚያደርግ በመሆኑ አስተዳደሩ አስፈላጊዉን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀው ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ትብብር እና ድጋፍ እንዲያበረክቱ ጥሪ አስተላፈዋል፡፡
    የድልጮራ ጄኔራል ሆስፒታል ለሕሙማንና ለጤና ባለሞያዎች በሚመጥን መልኩ ለማሻሻያ በሆስፒታሉ ላይ በጥናት የተለዩ ችግሮች እና ችግሮቹን ለመፍታት የተዘጋጀ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተካሄዶበታል
    የአገሪቱን የጤና አገልግሎት ሽፋን ከነበረበት እጅግ አነስተኛና ኢፍትሐዊ ደረጃ ለማሻሻል እና የሕዝቡን የጤንነት ሁኔታ በመቀየር እንዲቻል የህክሚና አገልግሎት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ “ሆስፒታሎቻችንን ለሕሙማንና ለጤና ባለሞያዎች በሚመጥን መልኩ የማሻሻያ ፕሮግራሙ ‹ያገባኛል› በሚል መርሕ የሚከናወን ነው። በ24 ሆስፒታሎች በዚህ ዓመት የሚመጀረው ይህ ፕሮግራም ሆስፒታሎችንን በማሻሻል፣ በማዘመንና ደረጃቸውን በማሳደግ ላይ የሚያተኩር ነው።