ድሬደዋ ዳግም ሁሉ የሚወዳትና የሚናፍቃት ከተማ ሆና ቀጥላለች!

    ድሬደዋና አሁናዊ ሰላሟ
    ከአንድ መቶ ሀያ አመታት በላይ የተሻገር እድሜ ያላት የበርሀዋ ንግስት የፍቅር ከተማ የሆነችው ድሬደዋ ካለፉት ሁለት አመታት በፊት ሰላሟ ከሷ ርቆ የሰላም አየሯ በረብሻ ግጭት ተቀይሮ ወትሮ ምድርና አፈሯ የተመቻቸው ነዋሪዎቿ ህልፈተ ህይወት የሚሰማበት አካላቸው የሚጎድልበት ለዘመናት በላባቸው ያፈሩት ንብረት ወደ ዶግ አመድነት የሚቀየርበት በሰላም ወተው ሰላም ስለመመለሳቸው እርግጠኛ መሆን ያልቻሉበት የደህንነት ስጋት የተጋረጠባት ከተማ ሆና ነበር::
    ይህ ይሁን እንጂ ይላላ ካልሆነ በቀር ፈፅሞ ተቆርጦ ሊወድቅ የማይችለው የከተማዋ ነዋሪ የአብሮነትና አንድነት ቋጠሮ ከየቱም ቅጥያ በፊትና በላይ ሰው ሰው በመሆኑ ብቻ በሰውነቱ በሰብአዊነት ሊከበር ሊወደድ አብሮ ከሌላው ጋር ሊኖት ይገባል የሚለው በዚሂ መርህ ላይ የተመሰረተው የነዋሪዎቿ የቀደመ የአብሮነት ህግጋትና ለዚህም መረጋገጥ ህዝቡ የከፈለው ዋጋ ጨምሮ የድሬደዋን ሰላም ወደ ቀድሞ ስፍራና ቦታ ለመመለስ የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽን ከመላው የከተማው ነዋሪ እንዲሁም ከሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ከመከላኪያ ከፌ/ፖሊስ ጋር በሰራው እጅግ አድካሚና እልህ አስጨራሽ ሰላምና ደህንነትን የማረጋገጥ ተግባራት እንሆ ዛሬ ላይ ከተማዋ የሰላም አየር መተንፈሷን ዳግም ቀጥላለች ::
    በዚህም የሀገራችን ክቡር ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምርቃትን ጨምሮ በዛሬው እለት ክብርት የኢ.ፊ.ድ.ሪ ፕሬዝዳንት ሳሀለወርቅ ዘውዴ የጉብኝትና ውይይት መድረክ እንዲሁም ክብሯን ሚንስትሮች፣የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች በተለያዩ ግዜያት የስራ ጉብኝት ሀገራዊ ውይይቶችና ስብሰባዎችን ሰላሟ በተመለሰው ድሬደዋ ከተማ ሲያካሂዱ በከተማዋ በዘንድሮ አመትም ብቻ ከ6 በላይ ሀገር አቀፍ የስፖርት ውድድሮች ሀገራዊና ክልላዊ ስብሰባዎችና ዝግጅቶች በአስተዳደር ደረጃ ከተካሄዱ በርካታ የአደባባይ ፕሮግራሞች ጋር ከተማችን ባላት ሰላም ተመርጣ በድምቀት ተካሂደዋል ::
    በዚህም ከስፖርት ቱሪዝምና የሆቴል ንግድ ገቢና እንቅስቃሴን ጨምሮ ሌሎች አሴቶችን ለከተማዋ መጨመር ማሳደግ ተችሏል::
    የድሬደዋ ከተማ ዛሬም ሆነ ነገ ይህ ሰላሟ ይበልጥ ተጠብቆና ቀጥሎ ለነዋሪዎቿ፣ለሀገራችን ህዝቦችና ለቀሪውም አለም ባለሀብቶችና አልሚዎች የተመቸችና ተመራጭ የሰላምና የፍቅር ምሳሌ ከተማ እንድትሆን የድሬደዋ ፖሊስ ሁል ግዜም ለሰላሙ ቅድሚያ ከሚሰጠው እገዛና ተሳትፎው ተኪ የለሽ ከሆነው የከተማው ህዝብና አስተዳደር ጋር በሰብአዊነት እያገለገለና በጀግንነት ሰላምና ደህንነትን እያረጋገጠና እያስቀጠለ የሚቀጥል ይሆናል::
    ድሬደዋ ከወንጀል ተግባርና ስጋት ነፃ ሆና ለነዋሪዎችና ለዜጎች የተመቸች ሁሉ የሚወዳትና የሚናፍቃት ተመራጭ ከተማ ሆና ትቀጥላለች።
    ምንጭ:-ድሬ ፖሊስ