በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ስር ለሚገኙ ለአራቱ ገጠር ፖሊስ ጣቢያ አባላቶች ለምግብነት የሚውሉ የተለያዩ ግብአቶች ድጋፍ ተደረገ፡፡

    የዋጋ ግምታቸው ከአንድ መቶ ሺብር በላይ የሚሆኑ ሀምሳ ኪስ ሩዝ፤ሀምሳ ደርዘን ፓስታ እና ሀምሳ ፍሬ የምግብ ዘይት ፤በገጠር ፖሊስ ጣቢያ በግዳጅ ላይ ለሚገኙ አባላት አዲል ጠቅላላ አስመጪ ድጋፉን ማድረጉ ታውቋል፡፡
    የአዲል ጠቅላላ አስመጪ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አዲል ይሳቅ ርክክቡን ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ከለውጡ በኋላ የከተማውን ሰላም እና ጸጥታ በማረጋገጥ ረገድ እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው በገጠር ፖሊስ ጣቢያ በግዳጅ ላይ የሚገኙ የፖሊስ አባላት ስራቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩ ለማስቻል ድጋፉን ሊያደርጉ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡
    ድጋፉን የተረከቡት የድሬዳዋ አስተዳዳር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ እንደገለጹት አቶ አዲል ያሲን በገጠር ፖሊስ ጣቢያ በግዳጅ ላይ ለሚገኙ የፖሊስ አባላት አስበው ድጋፉን ማድረጋቸውን አድንቀው የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ከመቼውም ጊዜ በላይ የከተማውን ሰላም እና ጸጥታ አስተማማኝ ለማድረግ እየሰራ መሆኑ እና በፖሊስ ላይ የህብረተሰቡ አመኔታ እየጨመረ መምጣቱ ይሄው ድጋፍ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
    የድሬዳዋ ፖሊስ የተጣለበትን ሰላምን የማረጋገጥ ተግባር ለመወጣት ተግቶ እንደሚሰራ ኮሚሽነር አለሙ ጨምረው ተናግረዋል፡፡
    ምንጭ፦ ድሬ ፖሊስ