የተፈጠረውን የኦክስጂን እጥረት ለማቃለል ባለሀብቶች ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል ተባለ፡፡
በድሬዳዋ ጤና ቢሮ የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ለሆነው የፈረንሳይ ሆስፒታል ክሮምቶ ማኑፋክቸሪንግ ፒልሲ 50 ኦክስጂን የተሞላባቸውን ሲሊንደሮች በድጋፍ አበርክቷል፡፡ በድጋፍ አሰጣጡ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ዕለት ተዕለት የኮቪድ-19 ስርጭት መጠን መስፋፋቱን ተከትሎ በአስተዳደራችን የህሙማን ቁጥርም በመጨመሩ ምክኒያት የተከሰተውን የኦክስጂን እጥረት ግምት ውስጥ በማስገባት ክሮምቶ ማኑፋክቸሪንግ ፒልሲ ላደረገው የኦክሲጂን ሲሊንደሮች ድጋፍ ምስጋናቸውን…


