ስፖርታዊ ውድድሮች ኢኮኖሚያዊ ፋይዳውን በማሻሻል የሀገር ልማት ላይ ከፍተኛ ፋይዳ እንዲኖረው ከማድረግ በዘለለ ለወጣቶችም የስራ እድል እንዲፈጥር መሰራት እንዳለበት ተገለፀ፡፡

    በድሬዳዋ አስተዳደር እየተካሄደ ለሚገኘው የቤትኪንግ ኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር መሳካት የጎላ ሚና ለነበራቸው አካላት የእውቅና ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡
    የ 2013 የቤትኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በድሬዳዋ አስተዳደር እየተካሄደ ይገኛል፡፡ 4 ተኛው ዙር የቤትኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ 13 ክለቦች ተሳታፊ ሆነው ውድድራቸውን እያካሄዱ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞም ውድድሩ በተሳካ ሁኔታ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋፆ ላበረከቱ የሚዲያ ባለሞያዎች እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት የእውቅና ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡
    የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ በዲኤስ-ቲቪ አማካኝነት ስርጭቱን አግኝቶ በመላው ሀገራችን እንዲሁም በአለማችን ላይ መተላለፉ ከጀመረ በኋላ በርካታ የእግር ኳስ ተመልካቾች ጨዋታዎችን መመልከት ከመቻላቸውም በዘለለ ውድድሩን ከቀን በዘለለ በምሽትም በማካሄድ በኢትዮጲያ እግር ኳስ ሌላ ታሪክ ማስመዝገብ መቻሉን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ከድር ጁሀር ተናግረዋል፡፡
    ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ከስፖርታዊ ውድድሮችና ውጤቶች ባሻገር እግር ኳሱን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳውን በማሻሻል የሀገር ልማት ላይ ከፍተኛ ፋይዳ እንዲኖረው ከማድረግ በዘለለ ለወጣቶችም የስራ እድል መፍጠር እንደሚገባ የድሬዳዋ አስተዳደር ሰፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሻኪር አህመድ ተናግረዋል፡፡
    ለውድድሩ መሳካት የጎላ ሚና ለነበራቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ፣ የፀጥታ አካላት ፣ ጋዜጤኞችና ፣ ለዲኤስቲቪ አባላት ከእለቱ የክብር እንግዶች ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡