አደጋው ቀበሌ 03 ልዩ ስሙ ሸመንተሪያ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መከሰቱን የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዲቪን ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ባንታለም ግርማ ተናግረዋል ።
አክለውም ከጠዋት ሁለት ሰአት ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ሰዓታት ዝናብ ሲጥል መቆየቱን በዚህም ሳቢያ እርዝመቱ 50 ሜትር የሆነ የግንብ አጥር በሶስት ቤቶች ላይ ተደርምሶ ከቀኑ ስድስት ከሀያ አካባቢ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ሞት ማስከተሉን የገለፁት ምክትል ኢንስፔክተሩ ከሟቾቹ ውስጥ የሶስት ወር ጨቅላ ህፃን ልጅን ጨምሮ የአምስ አመትና የሁለት አመት ታዳጊዎች እንደሚገኙበት አስረድተዋል።ሶስቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን ኢንስፔክተሩ አብራርተዋል።
በስፍራው ተመሳሳይ አደጋ እንዳይፈጠር ፖሊስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን ጠቁመው ሰሞኑን ከብሄራዊ ሜትሮሎጂ በተሰጠው ትንበያ መሰረት በቀጣይ ቀናትም ከባድ ዝናብ እንደሚጥል ስለሚጠበቅ ህብረተሰቡ ለንደዚህ አይነት አደጋ ሊያጋልጡ የሚችሉ ሁኔታዎችን በተቻለ መጠን እንዲከላከል ጥሪ አቅርበዋል


