የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ ባስተላለፉት የትንሳኤ በዓል የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸው ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል፡፡ አያይዘውም በዓሉ በሰላም፣ በፍቅርና በደስታ እንዲከበር ምኞታቸውንም ገልጸዋል፡፡ አክለውም እኛ ክርስቲያኖች በመገረፉ ቁስል የተፈወስን ከመከራ ስቃይ የዳንበት፤ ከወደቅንበት የተነሳንበት ልዩ በዓል በመሆኑ በዓሉን ስናከብር የተረሱ፣ የወደቁና ያዘኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማጽናናት፣ ያለንን በማካፈል እንዲሁም ደስታቸው ደስታችን እንዲሆን በማድረግ ሊሆን ይገባል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ወቅቱ በክርስትና እምነት ተከታዮች የአብይ ጾም ሲጾም የነበረበት እንዲሁም በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድም የታላቁ ረመዳን ጾም ላይ የሚገኙበት በመሆኑ እነዚህ ታላላቅ አጽዋማት መገጣጠም ለሀገራችን ሰላም መስፈንና አንድነት ምሳሌ ሊሆን የሚችል በመሆኑ በቀጣይም የሁሉም እምነት ተከታዮች ለሀገራችን ሰላም መስፈን የበኩሉን አስተዋጽኦ ሊወጣ ይገባል በማለት አቶ እስቅያስ ተናግረዋል፡፡
የፋሲካ በዓል ሲከበር አብሮ ተሰባስቦ የማክበር ሁኔታዎች ሊኖሩ ስለመችሉ የኮቪድ 19 ወረርሽን ታሳቢ በማድረግ አስፈላጊውን ሙያዊ ምክር ተግባራዊ በማድረግ ከኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ሁሉም እራሱን ሊጠብቅ እንደሚገባ አቶ እስቅያስ ታፈሰ ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም በዓሉን በመተሳሰብ በመደጋገፍና ያለው ለሌለው በማካፈል እንዲያከብር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡


