የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሐመድ ቡህ ለመላ የክርስትና እምነት ተከታዮች የትንሳኤ በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የጤና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገለጹ::

    የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሐመድ ቡህ ባስተላለፉት የትንሳኤ በዓል የመልካም ምኞት መግለጫ መልእክታቸው ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ ብለዋል፡፡
    ከንቲባው አያይዘውም በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የበረከት በዓል እንዲሆን የተመኙ ሲሆን ህዝበ ክርስቲያኑ በዓሉን ሲያከበር በኢትዮጵያዊነትና በድሬዳዋዊነት እሴቶቻችን የተቸገሩን የምናስብበት፣ የምንደጋገፍበትና በጋራ የምናከብረው መሆን ስላለበት የተቸገሩትን በመርዳት ሊሆን ይገባል በማለት ተናግረዋል፡፡ አቶ አህመድ መህመድ ቡህ አክለውም በዓሉ ሲከበር በመሰባሰብ እና በጋራ ማዕድ በመካፈል በመሆኑ የኮቪድ 19 ጉዳይን በተመለከተ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ሊሆን ይገባዋል፤ ምክንያቱም በቀጣይም ሌሎች በዓላትን ከዚህ ጊዜ በኋላ እንድናሳልፍና ለአገራችንም ሁላችንም ስለምናስፈልጋት ከኮረና ቫይረስ እራሳችንን መከላከል ይጠበቅብናል በማለት ጠቁመዋል፡፡
    በመጨረሻም ፈጣሪ ኢትዮጵያን እንዲጠብቃትና ሰላማችን እንዲበዛ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡