የኢ.ፌ.ድ.ሪ መከላከያ ሰራዊት ከሀገር ውስጥ ብሎም ከሀገር ውጪ የሚቃጣበትን ጥቃት ከመመከት ባለፈ ቀን ከለሊት የሀገሩን ዳር ድንበር በማስከበር ላይ ይገኛል ። ይህንንም ተከትሎ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው የህግ ማስከበር ተልእኮ ላይ ተሳትፈው ጉዳት ደርሶባቸው በምስራቅ እዝ ደረጃ ሶስት ሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኙ የሰራዊት አባላትን ማበረታታትና ከጉዳታቸውም አገግመው ወደ ግዳጅ እንዲቀላቀሉ ለማበረታታት ይቻል ዘንድ እንዲሁም የፌደራል ፖሊስ ፣ የምስራቅ አየር ምድብ የሰራዊት አባላት ፣ ከምስራቅ እዝ ጋር በጋራ በመሆን ድል በመፈፀማቸውና ነዋሪውም ህብረተሰብ ለሰራዊቱ ላደረገው ድጋፍ ለማመስገን ያለመ ፕሮግራም በምስራቅ እዝ ደረጃ ሶስት ሆስፒታል ተካሂዷል ።
በፕሮግራሙ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የምስራቅ እዝ ምክትል አዛዥ የሰው ሀብት ልማት ኮረኔል ሀሰን ሰኢድ የኢ.ፌ.ድ.ሪ መከላከያ ሰራዊት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ለተካሄደው የህግ ማስከበር ተልእኮ ላይ ድል ከማድረጉም በዘለለ የምስራቅ እዝ የአካባቢውን ሰላም ከማስጠበቅና ከማረጋገጥ አኳያ ሀላፊነቱን በሚገባ በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ተናግረው የሰራዊቱ አባላት ሀገራችንን ከስጋት ነፃ በማድረጋቸው ኩራት እንደተሰማቸውና ጉዳት የደረሰባቸው የሰራዊቱ አባላትም ከጉዳታቸው አገግመው ለተጨማሪ ግዳጅ እንደሚመለሱም ያላቸውን እምነት ተናግረዋል ።
በፕሮግራሙ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የሰራዊቱ አባላት በበኩላቸው የኢ.ፌ.ድ.ሪ መከላከያ ሰራዊት አባላት በተለያዩ ግንባሮች ላይ በመዝመት የሀገሩን ዳር ድንበር ከማስከበር ባለፈ እስከ ህይወት መስዋት መክፈል የሚያደርስ ጀግንነትን በመወጣት ላይ ለሚገኘው የሰራዊት አባላት እንደዚህ አይነት የድጋፍ ፕሮግራም በመካሄዱ እንዳስደሰታቸው ተናግረው ይህም ለቀጣይ ግዳጅ መነሳሳትን እንደሚፈጥርላቸውም ተናግረዋል ።


