የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የሁሉም ባለ-ድርሻ አካላት ርብርብን እንደሚጠይቅ ተገልፃል ።

    6 ተኛውን አለም አቀፍ የመንገድ ደህንነት ሳምንት አስመልክቶ ” መንገድ ለህይወት ” በሚል መሪ ቃል በፍጥነት ምክንያት እየደረሰ ያለውን የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ይቻል ዘንድ የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን የውይይት መድረክ አካሂዷል ።
    በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሀገራችን ላይ የትራፊክ አደጋ በብዛት እየደረሰ ይገኛል ። ከዚህም የትራፊክ አደጋ ጋር ተያይዞ በዜጎች አካል ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳትን እያከተለ ከመሆኑም በዘለለ የዜጎችን ህይወትም በመቅጠፍም ላይ ይገኛል ።
    ይኸውም የትራፊክ አደጋ እንደ ሀገርም ቢሆን በሚያሳድረው ተፅእኖ ምክንያት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችን በማስከተሉ ሳቢያ አሽከርካሪዎች በሚያሽከረክሩበት ወቅት የፍጥነት ገደባቸውን ጠብቀው በማሽከርከርና ዜጎችም እራሳቸውን ከትራፊክ አደጋ መጠበቅና መጠንቀቅ እንደሚገባና ከምንም በላይ ግን የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚጠይቅ በውይይቱ ላይ ተገልፃል ።
    በውይይቱ ላይም የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ቢሮ ሀላፊ ተወካዮች ፣ የፀጥታ አካላት ፣ የትራፊክ ፖሊስ እንዲሁም ባለ-ድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል ።