በከንቲባ አህመድ መሀመድ ቡሁ የተመራው የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራር ልኡክ በማሰልጠኛ የሚገኙ ምልምል ፖሊስ ሰልጣኛችን ጎበኘ:
ለስልጠናው ውጤታማነት አስተዳደሩ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልፆል::
ድሬ ፖሊስ:-
የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽን 12ኛ ዙር ምልምል ፖሊስ ሰልጣኞች ወደ ማሰልጠኛ ከገቡ አንድ ወር የሆናቸው ሲሆን የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራርም በማሰልጠኛው በመገኘት ጉብኝት አድርጎ ሰልጣኞችን አናግሯል:
ከጉብኝቱ መጠናቀቅ በሃል ንግግር ያደረጉት የድ/ዳ/አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡሁ ወደ ማሰልጠኛ ስንልካቹሁ ቤተሰባዊ ሃላፊነት ጭምር ወስደን እንደመሆኑ ለምርት ቀን ብቻ ሳይሆን የምንመጣው በስልጠና ላይም ተገኝተን መጠይቅ መደገፍ ሃላፊነት ስላለብን እየመጣን እንጠይቃችሃለን” ካሉ በሃላ ሰልጣኞች ባሳለፉት የአንድ ወር የስልጠና ግዜ የተሻለና ጥሩ የሚባል የስልጠና ግዜን ማሳለፋቸውን ለመገንዘብ እንደቻሉ ተናግረውል::
ከንቲባው ጨምረውም እንደተናገሩት ለድሬደዋ ሰላም መረጋገጥ ፖሊስ ኮሚሽኑ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት የሚደነቁ ናቸው ይሄም ተቋሙን በበቂ የሰው ሀይል ለማደራጀት ወደ ስልጠና ሰልጣኛች እንዲገቡ መደረጉ የዚሁ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል:: በቀጣይም እስከ ስልጠናው መጠናቀቅ ድረስ ለስልጠናው ውጤታማነት አስተዳደሩ ተገቢውን ድጋፍ በቅርበት እንደሚያደርግ በመግለፅ::
በእዚሁ ሰልጣኞችንና የስልጠናውን ሂደት ምልከታና ጉብኝት በተደረገበት መርሀ ግብር የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህን፣ ም/ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርን ጨምሮ የአስተዳደሩ ካቢኔ አባላት እና ኮሚሽነር አለሙ መግራ ተገኝተዋል::
ምንጭ፦ድሬ ፖሊስ


