የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መርሀ-ግብር አካሄደ ።
በሀገራችን የሚካሄደውን 6 ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ምክንያት በማድረግ የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ በለገሀር አደባባይ የምርጫ ቅስቀሳ መርሀ-ግብር አካሂዷል ።
በመርሀ-ግብሩ ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ መብራቴ ገብረየስ ብልፅግና ፓርቲ የለውጥ ፓርቲ ከመሆኑም በዘለለ ባለፈው ሁለት አመት በሀገራችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የለውጥ ስራዎች መሰራቱን ተናግረው በቀጣይም ብልፅግና ፓርቲ ሀገራችን ኢትዮጲያ ብሎም ድሬዳዋን ከተለያዩ የበለፀጉ ሀገራት ጋር በልማትና እድገት ተርታ ለማሰለፍ ከፍተኛ የሆነና ፈጣን እድገትን ሊያስመዘግብ የሚችል የፓርቲ ፕሮግራም ቀርፆ ስራ ላይ እያዋለ እንደሚገኝም አቶ መብራቴ ተናግረዋል ።
ብልፅግና ፓርቲ ባለፍት ጊዜያቶች በተለይም ለሴቶች እኩልነትና ተጠቃሚነት ብሎም ለሀገራችን እድገትና ብልፅግና ዘርፈ-ብዙ ስራዎች መስራቱን በመርሀ-ግብሩ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የፓርቲው ደጋፊዎችና አባላት ተናግረዋል ።
በድሬዳዋ አስተዳደር በተካሄደው የምርጫ ቅስቀሳ መርሀ-ግብር ላይም ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች እንዲሁም በከተማዋ ላይ ከሚገኙ 9 ኙም ቀበሌዎች የተውጣጡ የፓርቲው ደጋፊዎችና አባላት ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በእለቱም ብልፅግና ፓርቲ እንደ-ሀገር እየሰራቸው ያሉትን ስራዎች የሚያወድሱ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ በመርሀ-ግብሩ ላይ ታድመዋል


