በእለቱ 29 የሚሆኑ ታዳጊ የተማሪ ትራፊክ ፖሊሶችም ለምረቃ በቅተዋል፡፡
በስነ ስረአቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ እንደተናገሩት ማህበረሰቡ አማራጭ የሞተር አልባ ተሽከርካሪዎችንና የእግር ጉዞ ባህልን እንዲያጎለብት ገንዛቤን በመፍጠር እየደረሰ ያለውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ታስቦ መርሀግብሩ በትራንስፖርት ሚኒስትር እና በትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ትብብር ወር በገባ የመጨረሻው እሁድ እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል፡፡
በእለቱ መርሀግብርም በትምህርት ቤቶች አካባቢ በታዳጊዎች ላይ ሊደርስ የሚችለውን የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቀንሱ የታመነባቸው 29 ታዳጊ የትራፊክ ፖሊሶችን ላለፉት አራት ወራት በማሰልጠን ለምረቃማብቃት መቻሉንም ተናግረዋል፡፡
ትውልድ ላይ ሲሰራ ለውጥ ይመጣል ያሉት ዋና ዳይሬክሯ ይህን መሰረት በማድረግ ቅርንጫፍ ጽቤቱ በትምህርት ቤቶች ላይ ወርዶ እየፈጠረ ካለው የግንዛቤ ስራ በተጓዳኝ ታዳጊዎቹ መሰረታዊ የመንገድ ህንነት ህጎችን ባግባቡ ተረድተው ከትምህርታቸው ጎን ለጎን በትምህርት ቤቶቻቸው አካባቢ በመንገድ ማስተናበር ስራው እንዲሳተፉ ሰፊ ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡
በዋናነት በሚኒስተር መስሪያቤቱ ፈር ቀዳጅነትና አስተባባሪነት በሚዘጋጀው የሞተር አልባ ተሽከርካሪዎችና እግረኞች ቀን መርሀግብርም እንደ ድሬደዋ አስተዳደር በማህበረሰቡ ዘንድ ሰፊ የግንዛቤ ስራ መሰራቱንና በዚህም ለውጥ መታየቱን ተናግረዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሯ አያይዘውም አሁን ላይ ከምንግዜውም በላይ ስርጭቱ እየጨመረ የመጣው የኮሮና ወረርሽኝ ሌላ ስጋት ሌላ ፈተና ሀኗል ያሉ ሲሆን በተለይ ማህበረሰቡ ትራንስፖርትን ሲጠቀምም ሆነ አሽከርካሪው ሲያሽከረክር ማስክን ባግባቡ በመጠቀም ራሱን ከቫይረሱ እንዲታደግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ጉልማ ታዬ እንዲሁም ከድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽን ትራፊክ ዳይሬክቶሬት ተወካይ ኢኒስፔክተር ጌትነት ዳባ በመድረኩ ላይ ማህበረሰቡ በትራፊክ አደጋ እንዳይጎዳ ህግን አክብሮ መንገዱን ባግባቡ እንዲጠቀምና የሞተር አልባ ተሽከርካሪንና የእግር ጉዞን ባህል እንዲያደርግ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የእለቱ የክብር እንግዳና የተዘጋጀበት ቀበሌ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሀሰን በበኩላቸው መሰል መርሀግብሮች መዘጋጀታቸው ነዋሪዎች በመንገድ ደህንነት ህጎችና የሞተር አልባ ተሽከርካሪንና የእግር ጉዞን ባህል እንዲያደርግ በማስተማር ረገድ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጡ የተናገሩ ሰሆን እንደቀበሌያቸውም የእግረኛ መንገዶችን ከህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ነፃ በማድረግ ለእንቅስቃሴው ውጤታማነት የድርሻቸውን ለማበርከት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ ላይም የትራፊክ አደጋን አስከፊነትና የኮሮና ወረርሽኝን አስቀድሞ መከላከል ላይ ያተኮሩ መልእክቶችም ተላልፈዋል፡፡
በስተመጨረሻም ለተመረቂ ታዳጊ ትራፊኮችና ለአሰልጣኞች የእውቅና ሰርተፍ በመስጠትና በተመረጡ ጎዳናዎች ላይ የሳይክልና እግር ጉዞ በማካሄድ መርሀግብሩ ተጠናቋል፡፡
ምንጭ፦Federal Transport Authority Dire Dawa Branch


