ከቀናት በኋላ በሀገራችን የሚካሄደውን 6 ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ምክንያት በማድረግ የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ የከተማና ገጠር ቀበሌዎች የተለያዩ የምርጫ ቅስቀሳዎችን ሲያካሄድ ቆይቷል፡፡ የዚሁም አንድ አካል የሆነው የምርጫ ቅስቀሳና ለፓርላማ የሚወዳደሩ ዕጩዎችን የማስተዋወቅ ስራ በትላንትናው ምሽት በቀበሌ 08 በሚገኘው አስታጥቄ ሜዳ ላይ ዕጩዎችን የማስተዋወቅ ፕሮግራም የተካደ ሲሆን በዚሁም ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኋላፊ የሆኑት አቶ ከድር ጁሀር እንዳሉት ብልፅግና ፓርቲ ሀገራችን ኢትዮጲያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማላበስና የዲሞክራሲ ስርአትን ለመገንባት ላለፍት ሶስት አመታት በትጋትና በፅናት እየሰራ ተጉዞ በበርካታ ፈተናዎችና ውጣ-ውረዶች ተፈትኖ በጥንካሬ እዚህ ደረጃ የደረሰ ፅኑ ፓርቲ መሆኑን ተናግረው በተለይም ብልፅግና ፓርቲ ለመላው የኢትዮጲያ ህዝብ ህብረ-ብሄራዊነት የፍትህ መጎናፀፊያ በመስጠት ሁላችንንም የምትመስል የበለፀገች ጠንካራ ፌደራላዊ ኢትዮጲያ ለመገንባት እየሰራ የሚገኝ በሁሉም ለሁሉም የሆነ ፓርቲ መሆኑን ተናግረዋል ።
ሌላው በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ምክትል ሀላፊ የሆኑት አቶ ኡስማን አህመድ በበኩላቸው የብልፅግና ፓርቲ ፕሮግራሞች ሀገራችንን ከድህነት ፣ ህዝባችንን ከጉስቁልና ኑሮ እንዲሁም ወጣቶቻችንን ከስራ አጥነት ፣ ለማላቀቅ የሚያስችል ፕሮግራም ያለውና ለዚህም ተግባራዊነት በቁርጠኝነት የሚሰራና የሚተጋ ፓርቲ መሆኑን ተናግረው ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት አመታት የነዋሪውን ፣ የወጣቶችን ብሎም የሴቶችን ተጠቃሚነትና እኩልነትን ከማረጋገጥ አኳያ ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን መስራቱንና በቀጣይም ብልፅግና ፓርቲ ለሀገራችን ልማትና እድገት የተሻለ ስራን እንዲሰራ ከፓርቲው ጎን እንዲቆሙ ተናግረዋል ።
ለሀገራችን እድገትና ብልፅግና ጉዞ ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን እየሰራ ያለውን ብልፅግና ፓርቲን የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ብሎም የ 08 ቀበሌ ነዋሪዎች በመምረጥ ከብልፅግና ፓርቲ ጎን ሊቆሙ እንደሚገባ የቀበሌው ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ አዩብ አብዲ ተናግረዋል ፡፡


