ምስራቃዊ የእድገት ፋና የበጎ አድራጎት ማህበር 6 ተኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ለመታዘብ ለተመረጡ ታዛቢዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅቷል ።

    በ 2001 ዓ.ም የተመሰረተው ምስራቃዊ የእድገት ፋና የበጎ አድራጎት ማህበር በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ በከተማም ሆነ በገጠር ጤና ላይ ፣ ትምህርት ፣ ኤች.አይ.ቪ እንዲሁም የተለያዩ ማህበራዊ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።
    ምስራቃዊ የእድገት ፋና የበጎ አድራጎት ማህበር እያከናወናቸው ካላቸው ዘርፈ-ብዙ የማህበራዊ አገልግሎት ስራዎች በዘለለ የፊታችን ሰኞ የሚካሄደውን 6 ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ ምርጫው ሰላማዊና ፍትሀዊ በሆነ አግባብ ይካሄድ ዘንድ ምርጫውን ለመታዘብ የተመረጡ ታዛቢዎች በቂ የሆነ ግንዛቤ ይኖራቸው ዘንድ ምስራቃዊ የእድገት ፋና የበጎ አድራጎት ማህበር ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር 46 ለሚሆኑ ታዛቢዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅቷል ።
    6 ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊና ፍትሀዊ በሆነ አግባብ ይካሄድ ዘንድ ብሎም ምርጫው ተጀምሮ እኪጠናቀቅ ድረስ ለመታዘብ የተመረጡ 46 ለሚሆኑ ታዛቢዎች የስነ-ምግባር ደንብ ላይ ስልጠና መሰጠቱን የምስራቃዊ የእድገት ፋና የበጎ አድራጎት ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ግርማ ቱፋ ተናግረው በተለይም ለአንድ ሀገር እድገትና ብልፅግና ሰላም ከምን በላይ አስፈላጊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በቀጣይ በድሬዳዋ አስተዳደር በሰላም ዙሪያ የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት ማቀዳቸውንም ነው አቶ ግርማ ቱፋ በእለቱ የተናገሩት ።