በታሪካዊው ቀን ታሪክ እንስራ ሰኞ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም የድምፅ መስጫ ቀን ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ የሚወስኑበትና ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን የሚያረጋግጡበት ቀን ነው።

    ይህንን ታሪካዊ ቀን “ኢትዮጵያን እናልብሳት” በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ ያለውን 3ተኛውን የአረንገጓዴ አሻራ ቀን ምክንያት በማድረግ “ምርጫዬን እመርጣለሁ አረንገጓዴ አሻራዬን አኖራለሁ” በሚል መርህ በዚህ ታሪካዊ ቀን ታሪክ እንስራ ፡፡
    ስለሆነም መምረጥ ዲሞክራሲያዊ መብታችን ነው ችግኝ መትከል ግን ታሪካዊ ግዴታችን ፤ በመሆኑም በእለቱ ምርጫ እየመረጥን በነብስ ወከፍ 6 ችግኞችን በመትከል ኢትዮጵያን አረንገጓዴ በማልበስ በታሪካዊው ቀን ታሪክ እንስራ
    እያልን ጥሪያችንን እናሳተላልፋለን፡፡