ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ተሳታፊ የሆኑበት 3ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር በድሬዳዋ አስተዳደር ተካሄዷል ።

    በሀገራችን ኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ በሚገኘው 3 ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር 6 ቢሊዬን የሚሆኑ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን ይህም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር በድሬዳዋ አስተዳደር በከተማም ሆነ በገጠር እየተካሄደ ይገኛል ።
    በ 3 ተኛው የአረንጓዴ ልማት የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብርም በድሬዳዋ አስተዳደር 2 ሚሊዬን የሚሆኑ ችግኞችን ለመትከል የታቀደ ሲሆን የዚሁ ዕቅድ አንድ አካል በሆነውና የድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች እንዲሁም የቀበሌ አመራሮች ተሳታፊ የሆኑበት የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር ተካሂዷል ።
    በዚሁም መርሀ-ግብር ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ የአረንጓዴ ልማት የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብርን ምክንያት በማድረግ በአስተዳደሩ የሚገኙ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ለከተማው ብሎም ለአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ የሆነ ጠቀሜታ ያለውን የዛፍና የፍራፍሬ ችግኞችን መትከል መቻሉን ተናግረው በቀጣይም በአስተዳደሩ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የችግኝ ተከላው መርሀ-ግብር እንደሚካሄድና በዚሁም መርሀ-ግብር ላይ የአስተዳደሩ ነዋሪዎች በንቃት ተሳታፊ እንዲሆኑ እንደሚደረግም ነው አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ የተናገሩት ።
    በ 3 ተኛው የአረንጓዴ ልማት የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብርም በድሬዳዋ አስተዳደር 2 ሚሊዬን የሚሆኑ ችግኞች እንደሚተከሉና ከነዚህ ውስጥም ጥምር ደን 750 ሺህ ፣ የደን ዛፍ 1.2 ሚሊዮን ፣ እንዲሁም ሌሎች 50 ሺህ ችግኞች እንደሚተከሉና ይህም የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር መካሄዱ በተለይም ከምርጫ ማግስት እንደመሆኑ መጠን የፖለቲካ አመራሩ ለህዝቡ የገባውን ቃል የሚታይበት አንዱ ስራ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር እንደሆነ የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ተናግረው ከዚህ ቀደም በአስተዳደሩ በሚገኙና የመስኖ ገብ በሆኑ የገጠር አካባቢዎች ላይ የችግኝ ተካላዎች እንደተካሄዱና በቀጣይም የሀይማኖት አባቶች ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ፣ የፀጥታ አካላት እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ የሚሆኑበት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር እንደሚካሄድም አቶ ኢብራሂም ተናግረዋል ።