ድሬ ፖሊስ፦ሐምሌ 1/2013 ዓ.ም
በድሬዳዋ ከተማ ካለፉት ጥቂት አመታት ወዲሂ በተሰሩ ሰራዎች አመርቂ ዉጤት ከተመዘገገበባቸው ዉስጥ የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ በአስተማማኝ ደራጃ የማረጋገጥ ተግባር ዋንኛዉ ሲሆን ለዚህም መላዉን ህብረተሰብ ለሰላሙ ግንባር ቀደም ተዋናይ እንዲሆን መድረግ መቻሉ ለተገኘዉ ዉጤት ቀዳሚዉን ስፍራ ይይዛል፡፡
ክብርት የሰላም ሚኒስትሯም ይሄንኑ በድሬደዋ ከተማ መላዉ ህብረተሰብ በባለቤትነት ስሜት ከፖሊስ ጋር በመሆን በአካባቢ የሮንድ ጥበቃ ስራ እያከናወናቸዉ ያሉ ተግባራትንና ዞረዉ የተመለከቱ ሲሆን ከከተማዋ የለሊት ትራንስፖትር አገልግሎት ሰጪና የፀጥታ አገዥ ከሆኑ አሽከርካሪዎች ጋርም ዉይይት አካሂደዋል፡፡
ክብርት ሚንስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ከምልከታና ዉይይት ማጠናቀቂ ላይ እንደተናገሩት በማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት እንዲሁም ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመሆን ነዋሪዉ ህብረተሰብና ወጣቶች በእዚህ መልኩ ተደራጅታችሁ ለድሬደዋ ከተማም ሆነ ለሀገራችን ሰላም መረጋገጥ እየበረከታችሁት ያለዉ አስተዋፆ እጅግ በጣም የሚደነቅና የሚበረታታ ነዉ ለዚህም ምስጋና ላቀርብላችሁ ወዳለሁ ካሉ በሃላ በቀጣይም የድሬደዋ ከተማ ሰላሟ ተጠብቆ የፍቅር የመቻቻል የአንድነት ከተማ ሆና እንድትቀጥል ይሄዉ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ተግባራቹሁን አጠናክራቹ መቀጥል ይኖርባችኋል ብለዋል፡፡
በጉብኝትና ዉይይት መድረኩ ሀሳባቸዉን የገለፁ የህብረተሰብ ክፍልና አሽከርካሪ ወጣቶች በበኩላቸዉ ድሬደዋ ከጥቂት አመታቶች በፊት ሰላም ርቋት ረብሻና ሁከት እንዲሁም በትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይም ችግሮች ይፈጠርባት የነበረች ከተማ እንደነበረች አስታዉሰዉ ዛሬ ላይ ግን ፖሊስ እኛን መላዉ ህብረተሰብን በማሳተፍ በሰራቸዉ ስራዎች ሰላሟን ለመመለስ ችለናል ይህንንም በቀጣይ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል ብለዋል፡፡
በእዚሁ የፀጥታ አጋዥ የህብረተሰብ ክፍሎችን እንቅስቃሴ የመመልከትና የዉይይት መርሀ ግብር ክብርት ሚንስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ የድሬደዋ አስተዳደር ም/ከንትባ አቶ ከድር ጀዋር፣ኮሚሽነር አለሙ መግራና ሌሎች ሃላፊዎች በከተማዋ የተለያዩ መኖሪያ መንደሮች በአካል ተገኘኝተዉ ምልከታዉን አድርገዋል፡፡
ምንጭ፦ ድሬ ፖሊስ


