በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ የፀጥታ አካላት “የኢትዮጵያን እናልብስ-አረንጓዴ አሻራ” የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ተከናወነ።

    በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ የፍትህ (ፀጥታ) አካላት በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ የሚገኘውን ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ተሳታፊ በመሆን በድሬዳዋ አስተዳደር 04 ቀበሌ ቡትጂ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በከተማ ግብርና ዘርፍ በተሰማሩ አካላት ውስጥ አብደላ እርሻ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ለምግብነት የሚውል የፍራፍሬ ችግኞችን መትከል ችለዋል።
    የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በዘንድሮው ዓመት የምንተክለው ችግሩን መንግስት አንድም የእርሻ ማሳ ፆሙን እንዳይኖር በሚል በስቀመጠው አቅጣጫ መሰረርት የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ስጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በሌላ በኩል እየተከናወኑ ያሉ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ለአየር ንብረት ለውጥ ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባሻገር ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረው ተገልፃል።
    በመጨረሻም የኢፌድሪ ሰላም ሚንስትር ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል የሰላምና የፍቅር ተምሳሌት በሆነችው ድሬዳዋ ላይ ተገኝተው የአረንጓዴ አሻራቸውን ከሰላም ወዳዱ ህብረተሰብ ጋር በመሆን የአረንጓዴ አሻራቸውን በማኖራቸው የት ስማቸውን ደስታ ገልጸዋል ።
    በኘሮግራሙም በአስተዳደሩ የሚገኙ የፀጥታ አካላት እና በክረምት በጎ ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች በቦታው በመገኘት የ3ተኛውን የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።