በድሬዳዋ አስተዳደር በሸቀጣ ሸቀጦች ምርቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ መከሰቱን ሸማቾችና ነጋዴዎች ተናገሩ።

    የከተማ አስተዳደሩ በበኩሉ አላግባብ የሆነ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ነጋዴዎችና አከፋፋዮች ላይ እርምጃ መውሰዱንም አስታውቋል ።
    በድሬዳዋ አስተዳደር ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሸቀጣ ሸቀጥ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ እየተደረገ ይገኛል ። ከዚሁ የሸቀጣ ሸቀጥ ምርቶች የዋጋ ጭማሪ ጋር ተያይዞ በከተማዋ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ባሉ የመሸጫ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ መኖሩን ሸማቾችና ነጋዴዎች ተናግረው የሚመለከተው የመንግስት አካልም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አስመጪዎችና ነጋዴዎች ላይ አፋጣኝ የሆነ እርምጃ ሊወስድ ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል ።
    በድሬዳዋ አስተዳዳር ከተከሰተው የሸቀጣ ሸቀጥ ጭማሪ ጋር ተያይዞ አስተዳደሩ ከፍርድ ቤት ፣ ከጠቅላይ አቃቤ-ህግ ፣ ከፖሊስ ሚሽንና ከጉምሩክ ጋር በመሆንና በወያየት አላግባብ የሆነ የዋጋ ጭማሪ አድርገው የተገኙ 298 የሚሆኑ የንግድ ቤቶች መታሸጋቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ከድር ጁሀር ተናግረው ከዛ ውጪም ደግሞ 13 መጋዘን ፣ 3 ዳቦ ቤቶችና 7 አከፋፋዮች ላይም እርምጃ እንደተወሰደና በቀጣይም ተገቢውንና አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ የዋጋ ጭማሪውን የማስተካከል ስራ እንደሚሰራም አቶ ከድር ጁሀር ተናግረዋል ።