ድሬዳዋ ጀግኖቿን በክብር አመሰገነች ።
ከተማችን ድሬዳዋ አንጋፋና ስመጥር የሆኑ ስፖርተኞችን ማፍራት የቻለች ከተማ ነች ። ለአብነትም እነ ተካበ ዘውዴና ቢተው አብሬ በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሽ ናቸው ። በተለይም ተካበ ዘውዴ በክለብ ደረጃ ድሬዳዋ ከተማና ድሬዳዋ ጨርቃ ጨርቅ የተጫወተ ሲሆን በብሄራዊ ቡድንም ረጅም አመት በግብ ጠባቂነት ከመሰለፍ ባለፈ ሀገራችን ኢትዮጲያ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫን ባሸነፈችበት ወቅት በቡድኑ ውስጥ…


