በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ምክትል ፕሬዘዳንት አዘጋጅነት በዛሬው እለት በድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ ” ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አካባቢያዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ጂኦ ፓለቲካዊ ተፅዕኖዎች ” በሚል ርዕስ ሀገራዊ ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው ።
በዚሁም ኮንፍረንስ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህን ጨምሮ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ኡባህ አደም ፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ፕሮፌሰር አፎወርቅ ካሱ ፣ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተጋበዙ ፕሬዝዳንቶች ፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶች ፣ ምሁራን ፣ የዩኒቨርስቲው መምህራንና ተማሪዎች ፣ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ከተለያዩ የከተማ አስተዳደሩ የተጋበዙ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።


