በድሬዳዋ አስተዳደር 02 ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊትና ለልዩ ሀይል አባላት የሚሆኑ የስንቅ ማዘጋጀት ስነ-ስርአት እያካሄዱ ነው።

    የአሸባሪውን የህውሀት ጁንታ ቡድን ሀገርን የማፈራረስና የመበታተን የሽብር ተግባርና ተልእኮ የማምከንና ህግን የማስከበር ሀገራዊ ጥሪን ተከትሎ የኢ.ፌ.ድ.ሪ መከላከያ ሰራዊት እንዲሁም የልዩ ሀይል አባላት ህግን በማስከበሩ ግዳጅ ላይ ይገኛሉ ።
    ይህንንም ተከትሎ በድሬዳዋ አስተዳደር ልዩ ስሙ ሳቢያን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙ 22 መንደሮች ነዋሪውን በማስተባበር ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችንና ለልዩ ሀይል አባላት የሚሆኑ ስንቆችን በማዘጋጀት ላይ ይገኛሉ ።
    ከመከላከያ ሰራዊትና ከልዩ ሀይል አባላት ጎን መሆናቸውን ለመግለፅ ይቻል ዘንድ የስንቅ ዝግጅት በማዘጋጀት ላይ መሆናቸውን በድሬዳዋ አስተዳደር 02 ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች ተናግረው በቀጣይም በየወሩ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ ወደ ህግ ማስከበር ግዳጅ ድረስ በመሄድ ከመከላከያ ሰራዊትና ከልዩ ሀይል አባላት ጎን እንደሚቆሙም ተናግረዋል ።
    ከስንቅ ዝግጅቱ ጋር ተያይዞ በድሬዳዋ አስተዳደር 02 ቀበሌ ስር ባሉ 22 መንደሮች ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን በማስተባበር የስንቅ ዝግጅት ከማድረግ አንስቶ ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ የድሬዳዋ አስተዳደር 02 ቀበሌ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ወንድማገኝ በሻህ ተናግረው እስካሁን ባለው ሁኔታም ከ 450 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ በማዋጣትና የተለያዩ ድጋፎችን በማሰባሰብ ለመከላከያ ሰራዊትና ለልዩ ሀይላችን የሚሆኑ የስንቅ ዝግጅትና ሌሎች ስራዎችን በመሰራት ላይ እንደሚገኝም ነው አቶ ወንድማገኝ የተናገሩት ።
    ሀገራዊ የህግ ማስከበር ጥሪውን ተከትሎ በድሬዳዋ አስተዳደር 02 ቀበሌ የሚኖሩ 80 የሚሆኑ ወጣቶች በፍቃደኝነት ወደ ህግ ማስከበር ግዳጅ መዝመታቸውም ታውቋል ።