የቀበሌ 02 ነዋሪዎች ከ 750 ሺ ብር በላይ የሚገመት የስንቅ ድጋፍ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አበረከቱ።

    የአገራችንን ሉዓላዊነት ለማስከበር ከፍተኛ መስዋትነት እየከፈለ ለሚገኝዉ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችንና ለልዩ ሀይል አባላት ፍጆታ የሚሆን የተለያዩ የስንቅ እና የብር በድምሩ ከ750 ሺ ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አበረከቱ።
    በድጋፍ ርክክቡ ላይ የቀበሌ 02 ዋና ስራ አስፍፃሚ አቶ ወንድማገኝ በሻ እንደገለፁት የቀበሌዉ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊታችን ድጋፍ ለማድረግ ያላቸዉን ተነሳሽነት ከፍተኛ መሆኑን ገልፅዉ በቅርቡ መንግስት ይፋ ባደረገው ብሔራዊ ጥሪን ተከትሎ የተቋቋመው የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስተባባርነት የቀበሌዉ ነዋሪዎች አዋጥተዉ ያዘጋጅት ይህ ከ 750 ሺ ብር በላይ የሚገመት የስንቅ ድጋፉ ይበልጥ ተጠናክሮ እንድሚቀጥል አብራርተዋል።
    ድጋፍ ስነስርዓቱ ላይ የክብር እንግዳ ሆነዉ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር የመሬት ልማትና ማናጅመንት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ገበየሁ ጥላሁን ባደርጉት ንግግር እንዳሉት ሀገር ወዳድ ከሆነዉ ህዝባችን ጋር ሆነን ድል የማናድርገዉ እና ይማንሻገረ ችግር የለም ይህን ችግር ተሻግረን ታሪክ እናደርገዋልን ብለዋል።
    በድጋፍ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሀረር እና የድሬዳዋ የላይዘን ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት ኮሮኔል ዮናስ በብኩላቸዉ ጀግናው የመከላከያ ሰራዊትችን አገራችንን ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ የአሸባሪው የህወኅት ቡድንን ጨምሮ የሀገር ውስጥና የውጪ ጠላቶቻችንን ብሚገባ እየድመሰሰ እንደሚገኝ አብራርተዉ ህዝባችንን ጁንታዉ የህወኅት በማህበራዊ ገፆች በሚያሰራጫዉ የውሸት ፕሮፓገንዳዎች ሳይሽበር የህግ ማስከበር ዘመቻዉ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ በመቀጠል ሀገራችንን ከውስጥና ከውጪ ጠላቶች በጋራ ልናድን ይገባል ብለዋል።