የትምህርት ቤት ወርሃዊ ክፍያ ከ30% በላይ መጨመር እንደማይቻል ተገለፀ።

    በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የግል ትምህርት ቤቶች ለትምህርት አገልግሎት የሚያስከፍሉት ወርሃዊ ክፍያ ከ30% በላይ መጨመር እንደማይቻል ተገለጸ።
    በወቅታዊ የትምህርት ጉዳይ ላይ ያተኮረ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል
    የድሬዳዋ አስተዳደር ት/ቢሮ በወቅታዊ የትምህርት ጉዳይ ላይ በተለይም በግል ት/ቤቶች የዋጋ ጭማሪን በተመለከተ ዛሬ ለሚዲያ ተቋማት ቢሮው ባዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥቷል ።
    የቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ በቢሮአቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደ ገለጹት የግል ት/ቤቶች በየጊዜው በሚያደርጉት የዋጋ ጭማሪ ምክንያት ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን ቅሬታ መሠረት በማድረግ ቢሮው ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የግል ትምህርት ተቋማት ባለቤቶት ፣በሃይማኖት ተቋማት የተከፈቱ ት/ቤቶች እና የህዝብ ት/ቤቶችን የሚያስተዳድሩ አመራሮች ያሳተፉ የውይይት መድረኮ ሲካሄዱ ቆይተዋል።
    የግል ትምህርት ቤቶች ለሚሰጡት አገልግሎት ህብረተሰቡን ተመጣጣኝ ክፍያ በማስከፈል ለትምህርት ልማት እድገት የበኩላቸውን ድርሻ ማበርከት እንድችሉና ወላጆችም ለሚሰጣቸው የትምህርት አግልግሎት ተገቢውን ክፍያ እንድከፍሉ በሁሉም ትምህርት ቤቶ ፍትሃዊ የክፍያ አሰራር እንድኖር በማድረግ በየጊዜው ከህብረተሰቡ ለሚነሱ ቅሬታዎች ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት ቢሮው ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ ስንቀሳቀስ ቆይቷል።
    እንደ ኃላፊዋ ገለጻ በ2014.ዓ.ም ለግል ትምህርት ቤቶች ወርሃዊ የ ክፍያ ጭማሪ አስገዳጅ የሆኑ መሠታዊ ምክንያቶች ላይ ያጋራ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ከአስተዳደሩ ን.ኢ.ኢንቨ.ቢሮ ፣ ከትምህርት ቢሮ እና ከግል ትምህርት ቤቶች ማኅበር የተወጣጣ አንድ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ላለፉ ሁለት ወራት የዳሰሳ ጥናት ሲካሄድ ቆይቷል።
    ሁሉም የግል ትምህርት ቤቶች እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በተገኙበት የዳሰሳ ጥናት ውጤት የቀረበ ሲሆን በቀረበው የዳሰሳ ጥናት ውጤት መሠረትም የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የግል ትምህርት ቤቶት ለወርሃዊ የትምህርት አገልግሎት ክፍያ ቀደም ሲል ከሚያስከፍሉት ወርሃዊ ክፍያ እስከ 30 በመቶ ብቻ መጨመር እንደሚችሉ ከስምምነት ላይ ተደርሷል ።
    እንድሁም ለምዝገባ ከ25 % በላይ መጨመር እንደማይቻል ነው የተገለጸው ። በሁሉም የግል ትምህርት ቤቶች ፍትሃዊ የአገልግሎት ክፍያ ስርዓት በማስፈን በህብረተሰቡና በግል ትምህርት ቤቶች መካከል መልካም ግንኙነት እንድኖር የታመነበት ይህ የክፍያ ተመን በሁሉም ትምህርት ቤቶች እንድተገበር በቢሮውና ጉዳዩ በሚመለከተው የመንግስት አካላት ጥብቅ ክትትል እንደሚደረግ የገለጹት ሃላፊዋ ይህንን በማይቀበሉ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ በሽማቾች መብት ጥበቃ አዋጅ መሠረት ህጋዊ እርምጃ ይወሰድባቸዋል ብለዋል ።
    በሌላ በኩል የግል ትምህርት ቤቶች የብቃት ማረጋገጫ በመውሰድ ፍቃድ ለማሳደስ የሚጠበቅባቸውን የትምህርት ቤት እስታንዳርድ ከ 75% በላይ ማሟላት የሚጠበቅባቸው በመሆኑ ቢሮው በግል ትምህርት ቤቶች ላይ ባደረገው ክትትል ከእስታንዳርድ በታች ሆነው በተገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ የማስተካከያ እርምጃዎች መወሰዳቸውን የቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ በመግለጫቸው መጥቀሳቸውን ከትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።