በሃገር በቀል የሰላም እሴት ግንባታ እውቀት እንዲሁም ለዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ወሳኝ ሚና ያላቸው አካለትን ማዳበር ዙሪያ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሂዷል
መድረኩን በድሬደዋ ዩንቨርሲቲና የዮዝ ኤንድ ካልቸራል ዴቬሎፕመንት ፋውንዴሽን የጋራ ትብብት የተዘጋጀ ሲሆን የፋውንዴሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዜና ግርማ የማህበረሰቡን አጠቃላ ሰላም ለማስጠበቅ ዩንቨርስቲዎች እና ሲቪክ ማህበራት ወጣቶችን ማእከል ያደረገ የውይይት እና የምክክር መድረኮችን በስፋት ማካሄድ እንደሚገባቸው ገልፀዋል።
በዜጎች መካከል ሊፈጠሩ የሚችሉ ግጭቶችን ስር ሳየወሰዱ ለመቅጨት ሃገር በቀል የግጭት አፈታት እውቀቶችን ማበልፀግ እና በስፋት ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባም አቶዜና ጠቁመዋል።
የተለያዩ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላትን ባሳተፈው በዚህ መድረክ በርካታ ሃሳብ እና አስተያየት የተንሸራሸረ ሲሆን ሰላምና መልካም አስተዳደር እንዲሁም ዲሞክራሲያዊ ስረአትን ለማጠናከር የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያካተተ ተግባር ማከናወን እንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል።


