‹‹በአዲስ አመት የመረዳዳት በህላችን ዳብሮ የሚታይበት ሊሆን ይገባል››

    በ02 ቀበሌ በሃገር ውሰጥ እና ከውጭ አገር ያሉ የድሬደዋ ልጆች የሚመራው ቻይኒስቶና ነጻነት የእናቶችና አባቶች ምርኩዝ ማህበር ከሶስት መቶሺ ብር በላይ በሆነ ወጪ የዶሮ እንቁላል እና ሌሎች የአውዳመት ስጦታ ለሁለት መቶ አቅመ ደካማ ወገኖች አበርክቷል፡፡
    በድጋፍ ስነስረአቱ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኋላፊ አቶ ከድር ጁሃር ማህበሩ ላበረከተው ድጋፍ አመስግነው ይህ በጎተግባር በሁሉም የማህበረሰ በተለይም በወጣቶች ዘንድ መጎልበት አለበት ብለዋል።
    የድጋፉ አስተባባሪ ወጣት ነጻነት ጥላሁን ቻኒስቶና ነጻነት የእናቶች እና የአቦቶች ምርኩዝ የበጎ አድራጎት ማህበር በእንግሊዝ ሃገር የሚገኝው የድሬደዋ ልጅ አሸናፊ ተሻገር በተለያዩ የአለም ሃገራት እንዲሁም በሃገር ውስጥ ያሉ የድሬደዋ ተወላጆችን እና ወዳጆችን በማስተባበር አቅመ ደካሞችን የመደገፍ ተግባር በቋሚነት እንደሚያከናውን ጠቁሟል፡፡
    በተመሳሳ ዛሬም አድስ አመት እንደመሆኑ አቅመ ደካማ የሆኑ እናቶች እና አባቶች በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ሁለት ዶሮ ፤ ሶስት ሌትር ዘይት ፤ እንቁላል እና ሽንኩርት በጥቅሉ ለሁለት መቶ ወገኖች ድጋፍ መደረጉን ተናግሯል፡፡ከዚህ በተጨማሪ አራት ሰንጋዎችን በመግዛት በበዓሉ በጎዳና ላይ ላሉ ወገኖች ምሳ የማብላት ሂደት እንደሚኖርም አመላክቷል፡፡ የድጋፉ አጠቃላ ወጪ ሶስት መቶ ሺህ ብር እንደሚያወጣም ወጣቱ አስረድቷል፡፡
    ድጋፉ የተደረገላቸው ወገኖች ማህበሩ ከዚህ ቀደም ኮሮናናን ምክንያት በማድረግ ድጋፍ በማድረግ ከጎናቸው መቆሙን ጠቅሰው ዛሬም አዲስ አመትን አስታኮ በአሉን ደስ ብሎን እንድናከብር ላደረገልን እርዳታ ከልብ የመነጨ ምስጋናና አክብሮትን ለመሃበሩና ለወጣቶቹ እናቀርባለን ብለዋል፡፡
    በሌላበኩል የድሬደዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳች ቢሮ ሃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ በአገራችን እንዲሁም በከተማችን ድሬዋ በተለይ በወጣቱ ዘንድ የበጎነት ፤ የቅንንነትና የለጋሽነት ዝንባሌ እየዳበረ መሆኑን የሚሳዩ የተለያ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡እንደዚህ አይነቱ ተግባር ኢትዮጵዊ አንድነትን የሚጎለብት እንደመሆኑ መጠን ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ሲሉ አቶ እስቅያስ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡