የተቋሙ ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የበአል መዋያ ሚውሉ ሁለት ሰንጋዎች እና የገንዘብ ስጦታ አበርክተዋል፡፡
በስነስረአቱ ላይ በመገኘት ስጦታውን ያበረከቱት በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጨፍ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ እንደተናገሩት እስከህይወት መስዋትነት እየከፈሉ ሀገርን ለማስቀጠል ሚዋደቁ የሀገር ባለውለታዎቻችን በመሆናችሁ በአልን አብረን ነን ለማለት የእለቱን ድጋፍ አድርገናል ብለዋል፡፡
በቀጣይም ሚደረገውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው ዋና ዳይሬክተሯ የገለፁት፡፡ የምስራቅ እዝ ደረጃ ሶስት ሪፈራል ሆስፒታል አዛዥ የሆኑት ኮረኔል ብርሀኑ ዘውዴ በበኩላቸው የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የ 2014 ዓ.ም የአዲስ ዘመን መለወጫን ምክንያት በማድረግ የእርድ ከብት ድጋፍ በማድረጋቸው ምስጋናቸውን አቅርበው የድሬዳዋ አስተዳደር ብሎም የከተማው ነዋሪዎች እስካሁን ድረስ ከጎናቸው እንዳልተለየም ተናግረዋል ።
በዘውገ አውላቸው


