የአለም አቀፍ የቱሪዝም ቀንን ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት ተካሂዷል ።
በድሬዳዋ አስተዳደር በመካሄድ ላይ ያለው የአለም አቀፍ የቱሪዝም ቀን በዛሬው እለትም በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ የቱሪስት አገልግሎት ሠጪ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ማላቅ ላይ ትኩረት ያደረገ የፓናል ውይይት ተካሂዷል ።
በዚሁም የፓናል ውይይት ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሆኑት ወሮ ፈጡም ሙስጠፋ በተለይም ሀገራችን ኢትዮጲያ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች በጋራ የሚኖሩባት እንደመሆኗ መጠን የሀገራችንን የቱሪዝም መስህቦች ከባህላችን ጋር በማስተሳሰር የሀገራችንን ስልጣኔ የሚያሳዩ መስህቦችን የማስተዋወቁን ስራ ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረው በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሽታ ምክንያት በድሬዳዋ አስተዳደር በቱሪዝም ላይ የነበረውን ጫና ለመቋቋም ይቻል ዘንድ በኮቪድ ፕሮቶኮል መሰረት ከአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በተለያየ ወቅት ወደ ከተማችን የቱሪስት መስህቦችን ለማየት የሚመጡ እንግዶችን የሆቴልና የቱሪዝም ኢንዱስትሪ የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ አስተዳደሩ ለባለሀብቶች ድጋፍ በማድረግ የከተማዋን ኢኮኖሚ ለማሳደግ በመስራት ላይ እንደሚገኝም ወሮ ፈጡም ተናግረዋል ።
34 ተኛውን የቱሪዝም ቀን ሲከበር የፅዳት ፣ የችግኝ ተከላ ፣ የብስክሌት ግልቢያ ፣ የፓናል ውይይት ፣ የኪነ-ጥበብ ምሽትና የታሪካዊ ቦታዎች ጉብኝት በማካሄድ የከተማችንን የቱሪስት መስህቦች ማስተዋወቅ እንደሆነ የድሬዳዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙራድ በደዊ ተናግረው ይህም በዋናነት የማህበረሰቡን ግንዛቤ ለመፍጠርና የድሬዳዋን ገፅታ ለመገንባት መሆኑንም አቶ ሙራድ በደዊ ተናግረዋል ።
በዚሁ የፓናል ውይይት ላይ የኢ.ፌ.ድ.ሪ የባህልና ቱሪዝም የቱሪዝም ሚኒስቴር ዲኤታ የሆኑት ክብርት ወ\ሮ ቡዜና አልከድርን ጨምሮ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ አባገዳዎች ፣ ኡጋዞች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በቀጣይም የከተማው የሚገኙ መስህቦች ጉብኝት ፣ የባቡር ሽርሽር እንዲሁም የምስጋናና የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር የሚከናወን ይሆናል።


